Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 11, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከአለም ባንክ ግሩፕ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር Dr Zarau Wendeline Kibwe ጋር ተወያይቷል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት በመንግስት እየተተገበረ ባለው የመንግስት የማክሮ ኢኮኖሚክ ሪፎርም አፈፃፀም ፣ በአለም ባንክ ድጋፍ በትግበራ ላይ የሚገኙ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም ባንኩ በቀጣይ ከአገራችን ጋር በሚኖረው የልማት የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ የግሉ ዘርፍ ሚና እና ተሳትፎ ምን መሆን እንደሚገባው ከአለም ባንክ ግሩፕ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር Dr Zarau Wendeline Kibwe ጋር ተወያይቷል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ም/ቤቱ በአገሪቷ እየተተገበር ሪፎረም ጋር እራሱን ለማጣጣምና የግሉን ዘርፍ ከሚጠብቀው ብርቱ ፉክክር አንፃር ዝግጁ ለማድረግ መሰረታዊ የሆን የሪፎረም ስራ ተግባራዊ ማድረጉንና ይህንንም እውን ለማድረግ መዋቅራዊ ለውጥ በማካሄድ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን አስረድተዋል፡፡

የም/ቤቱ ራዕይ በቀጣይ ሁለት የስትራቴጂክ ዕቅድ አመታት ውስጥ የግሉ ዘርፍ በአገሪቱ የጂዲፒ ዕድገት ውስጥ የሚኖረው ድርሻ የመሪነቱን ስፍራ እንዲኖረው ነው ያሉት ዶ/ር ቀነኒሳ፣ ለዚህ ዕውን መሆን ደግሞ የአጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ስለሆነም አለም ባንክ የኢትዮጵያን የግል ዘርፍ አቅም ለመገንባትና ም/ቤቱ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአለም ባንክ ግሩፕ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር Dr Zarau Wendeline Kibwe በበኩላቸው የትዮጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ዘርፎቹን ለውጭ አገራት ክፍት በማድረጉ የኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ለሚጠብቀው ብርቱ ፉክክር እራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ገልፀው የአለም ባንክ ወሳኝ በሆኑ ሴክተሮች በተለይም ከሚፈጥሩት የስራ ዕድል አንፃር ለግብርና፣ ቱሪዝም፣ ጤና (የህክምና ቁሳቁሶችና መድሁኒቶችን ማምረት)፣ ለማኑፋክቸሪንግና መሰረተ ልማቶች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ አስረድተዋል፡፡ በእነዚህ ዘርፎች ውስጥ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማደግ እነዳለበትም አሳስበዋል፡፡

   
The Ethiopian Chamber of Commerce and Industry discussed with Dr. Zarau Wendeline Kibwe, Executive Director of the World Bank Group, the implementation of the government’s macroeconomic reform, the projects and programs being implemented with the support of the World Bank, and the role and participation of the private sector in the future development focus of our country.

The Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Association Dr. Kenenisa Lami (Associate Professor), explained that the chamber has implemented fundamental reform work to align itself with the reforms being implemented in the country and to prepare the private sector for the fierce competition that awaits it. To achieve this, it has prepared and implemented a five-year strategic plan by implementing structural changes.

Dr. Kenenisa said that the vision of the Chamber is for the private sector to play a leading role in the country’s GDP growth over the next two strategic plan years, and that the support of partner organizations and stakeholders is crucial for this to happen. Therefore, he called on the World Bank to support the Chamber’s efforts to build the capacity of the Ethiopian private sector and to build the capacity of the Chamber.

World Bank Group Executive Director Dr. Zarau Wendeline Kibwe, for his part, said that the Ethiopian government should prepare itself for the intense competition that the Ethiopian private sector faces by opening up its economic sectors to foreign countries.

He explained that the World Bank will pay special attention to critical sectors, especially agriculture, tourism, health (production of medical supplies and medicines), manufacturing, and infrastructure, in terms of job opportunities they create. He also stressed the need to increase private sector participation in these sectors.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia