Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 15, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከትሬድ ማርክ አፍሪካ ጋር አብሮ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያየ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከትሬድ ማርክ አፍሪካ ጋር አብሮ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያየ፡፡

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምከር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የተመራው የማኔጅመንት ቡድን ከትሬድ ማርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ እውነቱ ታዬ ጋር በጽህፈት ቤታቸው በሁለትዮሽ ሊሰሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ቀደም ሲል በአንድ መስኮት አገልግሎት ትግበራ ላይ ከአፍሪካ ትሬድ ማርክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ አገልግሎቱን በድጂታል መስጠት በመቻሉ ከማዘመኑም ባሻገር አገልግሎት ፈላጊ የንግዱን ማህበረሰብ ጊዜና ወጪ ለመቆጠብ ማስቻሉን አስረድተው፣ ለዚህም በም/ቤቱ ስም አመስግነዋል፡፡

ለወደፊቱም ም/ቤቱ ትኩረት አድርጎባቸው የለያቸውን የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ሊያሻሽሉና አቅማቸውን ሊገነቡ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በፋይናንስ እንዲደግፉ ለዳይሬክተሩ ጥያቄአቸውን አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት አሁን ላይ ከወትሮው በተሻለ ሁኔታ የግሉን ዘርፍ ፍላጎት ለማሟላትና ከመንግስት ጋር ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነት ለማሳለጥ፣ እየመጣበት ባለው ብርቱ ፉክክር ውስጥ ጠንካራ ተወዳዳሪ እንዲሆን እየሰራ ነው ያሉት ዋና ፀሐፊው ለዚህ ደግሞ የአጋር ድርጅቶች እገዛ ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

የትሬድ ማርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ እውነቱ ታዬ በበኩላቸው ቀደም ሲል የፋይናንስ ድጋፍ የተደረገለት የአንድ መስኮት አገልግሎት አሁን ያለበት ሁኔታ አስደሳች መሆኑን ገልፀው ሌሎች በም/ቤቱ ተቀርፀው የፋይናንስ ድጋፍ የሚጠየቅባቸው ፕሮጀክቶች በለጋሽ ድርጅቶች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ በቀጣይነታቸው፣ በሚያመጡት አዎንታዊ ለውጥና ም/ቤቱ ፕሮጀክቶቹን በባለቤትነት ተግባራዊ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት በደንብ የሚገልፁ መሆን እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡

በዚህ መሰረት ለሚቀርቡ ፕሮጅክቶች በተቻለ መጠን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አሳውቀዋል፡፡

   

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia