Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 07, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሣ ለሚ ( ተባባሪ ፕሮፌሠር) በኢትዮጵያ ከአዘርባጃን አምባሣደር ሩስላን ናሲቦቭ ጋር ተወያዩ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሣ ለሚ ( ተባባሪ ፕሮፌሠር) በኢትዮጵያ ከአዘርባጃን አምባሣደር ሩስላን ናሲቦቭ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ሥላለው የንግድና ኢንቨሥትመንት ልውውጥ እንዲሁም ሥላሉ መልካም አጋጣሚዎች ተነጋግረዋል። አምባሣደር ሩስላን በተለይም ሀገራቸው በአፍሪካ ለሚኖራት የንግድና ኢንቨሥትመንት ኢትዮጵያን ዋነኛ ቀዳሚ መዳረሻ መግቢያ ለማድረግ ተመራጭ መሆኗን ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊው ዶክተር ቀነኒሣ በኢትዮጵያ ሥላለው ምቹ የንግድና ኢንቨሥትመንት ሁኔታ እንዲሁም ምክር ቤቱ እየሠራቸው ባሉ ሀገራዊ የንግድና ኢንቨሥትመንት እንዲሁም የአቅም ግንባታና ሌሎች ሥራዎች ዙሪያ አብራርተውላቸዋል።

የአዘርባጃን የወጭ ንግድና ኢንቨሥትመንት ፕሮሞሽን-አዝፕሮሞ ምክትል ኮሚሽነር ቱራል ሀጂሊ የኢትዮጵያ- አዘርባጃን እንዲሁም የአፍሪካ – አዘርባጃን የኢኮኖሚ ፎረም በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ፍላጎት እንዳላቸውም አንሥተዋል።

በሁለቱ ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባም ነው በውይይቱ የተጠቆመው።

የአዘርባጃን የወጭ ንግድና ኢንቨሥትመንት ፕሮሞሽን-አዝፕሮሞ ተወካይ ሳቢር ዘይናሊ እንዲሁም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia