Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 04, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመተባበር የተቋቋመው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማሥተባበሪያ ክፍል በይፋ ስራዉን ጀመረ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመተባበር የተቋቋመው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማሥተባበሪያ ክፍል በይፋ ስራዉን ጀመረ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እንዲሁም ከጅአይዜድ (GIZ) ጋር በመተባበር ነው ማሥተባበሪያ ክፍሉ የተቋቋመው።

በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ተሻለ  በሬቻ፣ የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት፣ የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳዊት ሞገስ፣ የጂአይዜድ GIZ) STEP ማናጀር ሞሀመድ አሊ ካሃንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ( ተባባሪ ፕሮፌሠር) ማስተባበሪያ ክፍሉ በኢንዱስትሪውና  በሥልጠና ተቋማት መካከል ያለውን የሠለጠነ የሠው ኃይል ፍላጎትና አቅርቦት የተሻለ፣ በፍላጎት ላይ የተመሠረተና ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ሞሀመድ አሊ ካሃን በበኩላቸው በቴክኖክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ውጤት ለማምጣት የግሉ ዘርፍ ተሣትፎ በእጅጉ አሥፈላጊና ሊተካ የማይችል መሆኑን ገልጸው አሁን የተከፈተው የማሥተባበሪያ ክፍል ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia