የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በመተባበር የንግዱን ማኅበረሰብ መሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻዎችን ባሳተፈ መልኩ በአዲስ አበባ ተካሄደ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ፤ የግሉ ዘርፍ ሚና በሀገራዊ ምክክር ሂደት ፤ በሚል መሪ ርዕስ ያዘጋጁት መድረክ የኮሚሽኑን አመራሮች፣ የንግዱን ማኅበረሰብ መሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻዎችን ባሳተፈ መልኩ በአዲስ አበባ ተካሄደ።
እንደሚታወቀው፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአገር ውስጥ እንዲሁም በውጪ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለመግባባት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በህዝባዊ ውይይት ሰብስቦ በሀገር አቀፍ ደረጃ ምክረሃሳብ የሚያሰናዳበትን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ያካሂዳል።
ለዚህ ታሪካዊ ሀገራዊ የምክክር ውጤታማነትም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ወሳኝ ከመሆኑ አንፃር በመላው ኢትዮጵያ በተደረጉ የአጀንዳ ማሰባሰብ ተግባራት እንደባለድርሻ አካል የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ምክር ቤታችንም መምከር :- ለሰላም፣ መከባበር እና አንድነት ለንግድ እና ኢንቨስትመንት መስፋፋት ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ስንሰራ ቆይተናል ።
የዛሬው መድረክም ፤ የዚህ ጥረታችን አንድ አካል ሲሆን ፤ ዓላማውም ሰላም ከፖለቲካ አውድ ፍቺው ባሻገር ለንግድ እንዲሁም ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት(FDI) ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ ከመሆኑ አንፃር ፤ የሁላችንም ትኩረት እንዲሆን ለማስቻል እንዲሁም ለምክክሩ ስኬት ለግሉ ዘርፍ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን የጋራ ግንዛቤን ለማጠናከር ጭምር ነው።
በውይይቱም የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና ኃላፊዎች እንዲሁም የክልሎች የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንቶችና ዋና ጸሐፊዎች በተጨማሪም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ከመሆኑ አንፃር ከላይ ካነሳሁት ቁልፍ ጉዳይ እና ከሚቀርበው የውይይት መነሻ ፅሑፍ በተጨማሪ ከየአካባቢያችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ እምነቴ ነው።
በመጨረሻም መድረኩ እንዲሳካ ላደረገው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሸን እንዲሁም ድጋፍ ላደረጉልን ተቋማት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት

Today, the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, in collaboration with the Ethiopian National Dialogue Commission, is conducting a forum in Addis Ababa under the theme “The Role of the Private Sector in the National Dialogue Process.” The event has brought together the Commission’s leadership, leaders of the business community, and other key stakeholders.
As is well known, the Ethiopian National Dialogue Commission will undertake a nationwide National Dialogue Conference.
Given the critical importance of private sector participation to the success of this historic national dialogue, the private sector has been actively engaged as a stakeholder in agenda setting activities conducted throughout Ethiopia. Likewise, our Chamber has consistently devoted attention to this issue, recognizing that peace, mutual respect, and national unity play a vital role in expanding trade and investment.
Today’s forum is part of these ongoing efforts. Its objective is to emphasize that peace is not only a political concept but also a key prerequisite for trade, domestic investment, and Foreign Direct Investment (FDI).
The forum seeks to ensure that this issue receives the attention it deserves and to strengthen a shared understanding that the success of the national dialogue is essential for the growth and development of the private sector.
The discussion is attended by officials of the Ethiopian National Dialogue Commission, members of the Board of Directors and heads of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, Presidents and Secretaries General of Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, as well as invited guests. I am confident that, in addition to the key issues I have highlighted and the discussion paper to be presented, participants will engage in a broad and constructive dialogue reflecting the realities and experiences of their respective localities.
Finally, I would like to express my sincere appreciation to the Ethiopian National Dialogue Commission for its contribution to the successful organization of this forum, as well as to all institutions that have supported us in making this event possible.
Sebsib Abafira Abajobir
President, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

