የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከፈረንሳይ የልማት ትብብር ተቋም (AFD) ECOTRADE ፕሮጀክት ተወካዮች ጋር ተወያየ፡፡


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከፈረንሳይ የልማት ትብብር ተቋም (AFD) ECOTRADE ፕሮጀክት ተወካዮች ጋር ተወያየ፡፡
ሁለቱ አካላት በንግድና ቀጣናዊ ውህደት፣ በእሴት ሰንሰለት ልማት፣ በንግድ ማሳለጥና ማስተዋወቅ፣ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ነው የተወያዩት፡፡
በኣውሮፓ ኅብረት እና በፈንሳይ የልማት ትብብር ተቋም (AFD) የሚተገበረው « Promoting Ethiopian trade and economic integration through private-led value chains development” ፕሮጀክት በቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር፣ በንግድ ማሳደግ እና ቀጣይነት ያለው እድገት ማምጣት፣ በስራ እድል ፈጠራ እና በአካባቢ ልማት በኢትዮጵያ ያሉትን እድሎች በማልማት ላይ እንደሚያተኩር የፕሮጀክቱ ቡድን መሪ ሜሮን ዳኛው ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱም በፕሮጀክቱ ትግበራ ውጤት ለማምጣት ከግሉ ዘርፍም ሆነ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርን ጨምሮ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር እንደሚሰራ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ በውይይቱ ላይ አንስተዋል፡፡
ይህ ECOTRADE የተሰኘው ፕሮጀክት በቅርቡ በይፋ ስራውን ሲጀምር የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ውጤታማ ለማድረግ በተለይም በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የእሴት ሰንሰለት፣ በአቅም ግንባታ፣ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ማዕቀፍ፣ በፕሮቶኮል፣ ገበያ በህግ ጉዳዮች እና በመሳሰሉት ላይ ውጤታማ ስራ እንደሚሰራ በውይይቱ ተብራርቷል፡፡

