Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 21, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ልዑካን ቡድን ከሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማንፋራህ ጋር ተወያይቷል።

 

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ተመርቶ ለሁለት ቀናት የስራ ጉበኝት ወደ ሶማሌ ክልል የተጓዘዉ የምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ልዑካን ቡድን ከሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማንፋራህ ጋር ተወያይቷል።

በዉይይቱም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ከምክር ቤቱ ታሪካዊ ዳራ በመነሳት ዛሬ ያለበትን ሁኔታ እና ተልዕኮዉን አብራርተዋል።

በተለይም አሁን ላይ የኢትዮጵያ  ነጋዴዎች እየመጣባቸዉ ካለዉ ብርቱ ፉክክር አንፃር ተወዳዳሪ ሆነዉ ለመዉጣት በተደራጀ መልኩ መንቀሳቀስ ዘመኑን የዋጀ ዕዉቀት መታጠቅ እንዳለባቸዉ ገልፀዉ ለዚህ ደግሞ በየደረጃዉ ባሉ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት አባል መሆን አለባቸዉ።

የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምንም እንኳን የግሉ ዘርፍ ድምፅ ቢሆኑም የንግዱ ማህበረሰብ መንግስት በሚያወጣቸዉ የህግ ማዕቀፎች ዉስጥ ህጋዊ ንግድ በመስራት የሚጠበቅባቸዉን ህጋዊ ግብር እንዲከፍሉ በማድረግና ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የሚያደርግ የመንግስት ቀኝ እጅ ነዉ ለማለት ይቻላል።

ስለሆነም የሶማሌ ክልል በንግድ መዳረሻነቱ ከጎረቤት ክልሎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከጎረቤት አገሮች ጋርም ጠንካራ የንግድ ትስስር ስላለዉ የንግዱን ማህበረሰብ የሚያሰባስብ ጠንካራ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያስፈልገዋል።

ለዚህ ደግሞ የክልሉ መንግስት ለሶማሌ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ተገቢዉን ድጋፍ እንዲያደርግና እንዲያበረታታ አቶ ሰብስብ ለምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ጥያቄአቸዉን አቅርበዋል።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማንፋራህ  በበኩላቸዉ የክልሉ መንግስት በክልሉ የንግድ ስራዉ በተደራጀ መልኩ እንዲመራ ምክር ቤቱ እንዲጠናከር እንደሚፈልግ ገልፀዉ እኛም እንደክልላዊ መንግስት ተገቢዉን ድጋፍ እናደርጋለን፤  የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤትም ድጋፍና ክትትል ማድረግ አለበት ብለዋል።

   

በአሁኑ ወቅትም የክልሉ መንግስት ለክልሉ ንግድና ዘርፍ ማኅ      በራት ምክር ቤት የራሱ ህንፃ መስርያ ቦታ ለመስጠት እያመቻቸ መሆኑንም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

ከለዉጡ ወዲህ በክልሉ በተረጋገጠዉ ፍፁም ሰላም በአሁኑ ጊዜ  ሁሉም ሊኖርበት የሚመኝ ክልል ሆኗል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከዚህ ቀደም ያልተለመደ የግብርና ስራም ተጀምሯል ብለዋል።

አሁንም ሰፊና ሊለማ የሚችል መሬት ስላለን በዘርፉ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸዉን እንዳያፈሱና ለዚህም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አምባሳደር ሆኖ እንዲያስተዋዉቅ ጥሪ  አቅርበዋል።

በዉይይቱ ላይ የሶማሌ ክልል የንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀሰን የሱፍ፣  የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ አቶ ከማል ሼህመሀመድ  እና የሱማሌ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ሀሰን ሸርማርኬ እና ሌሎች የቦርድ አባላት ተገኝተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia