Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፤ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፤  በጎፋ ዞን  በደረሰው  የመሬት መንሸራተት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች  የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ለተጎጂ ቤተሰቦችም መፅናናትና  ብርታትን   ተመኝተው ድጋፉን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያስረከቡት የምክር ቤቱ  ም/ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐይናለም አባይነሕ እና ዋና ፀሐፊው ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ናቸው።

ዶክተር ዐይናለም አባይነሕ በርክክቡ ላይ እንደተናገሩት አደጋው በደረሰ በማግስቱ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት አቶ ሰብስብ አባፊራ በምክር ቤቱ እና በራሳቸው ስም በአዳጋው ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ሀዘናቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ከጉዳቱ የተረፉ ቤተሰቦችን መልሶ ማደራጀት እንዲቻልም የንግዱ ህብረተሰብ ኃላፊነቱን በየደረጃው እንዲወጣ ጠይቀዋል ብለዋል።

እክለውም፤ ከጉዳቱ የተረፉ ቤተሰቦችን፤ በተፈጥሮ አደጋው የተጎዳውን አካባቢና ህብረተሰቡን በቋሚነት መልሶ ለማቋቋም የሚሰራው ስራ የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ  በተለያዩ አካለት ድጋፍ ሲደረግ የቆየ ሲሆን፤ የኛም በዚህ ስፍራ መገኘት በዋነኛነት  በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን ባለን አቅም ለመደገፍ ፤ ከዚያም በላይ ግን ሀዘናችሁን ለመጋራትና የንግዱ ማኅበረሰብ ከጎናችሁ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው ብለዋል።

ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸው በተከሰተው የመሬት መንሸራተት በደረሰ አደጋ ሕይወታቸውን ካጡ ሰዎች ውጪ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ቤተሰቦች አሉ፤ እነዚህን አካሎቻችንን በቦታው በመገኘት ማጽናናት እና መልሶ እንዲቋቋሙ ማድረግ፤ ከዚህ ባለፈ ደግሞ የሚፈጠረውን ማህበራዊ ቀውስ ለመቀነስና በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ብሎም መልሶ ማደራጀት እንዲቻል አሁን ካደረግነው የ300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ ባሻገር መላው የንግዱ ማኅበረሰብ ኃላፊነቱን በየደረጃው እንዲወጣ የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia