Feb 26, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በዲጂታል አገልግሎት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡
በተግባር በታገዘው በዚህ ስልጠና ምክር ቤቶች እና አባል ማኅበራት የአባላትን መረጃ በተደራጀ የዲጂታል አገልግሎት እንዲይዙ እንዲሁም የሚሰጧቸው አገልግሎቶች በኦንላይን መሆን እንዳለባቸውና ይህም የተቀላጠፈ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የተደራጀ መረጃ ለመያዝ እንደሚያግዝ በስልጠናው ላይ ተገልጧል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የምክር ቤቱ የአይ ሲቲ ዲቪሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሀርያ ወልደገብርኤል እና የአይሲቲ ባለሙያው አቶ ኤርምያስ አባይ ናቸው፡፡
በGIZ-SEQUA የገንዘብ ድጋፍ በምክር ቤቱ የቢዝነስ አመራር አካዳሚ የተሰጠው ይህ ስልጠና በቀጣይም እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

