Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ተወያየ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ተወያየ፡፡

ምክር ቤቱ የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ የመሪነት ሚና ለመወጣትና በመንግስትና በግሉ ሴክተር መካከል እንደ ድልድይ በመሆን የሚሰራ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ይሰራል፡፡

ስለሆነም ምክር ቤቱ የሚሰራቸውን ስራዎች የበለጠ ለማጠናከርና ለንግዱ ማህበረሰብ ምቹ የቢዝነስ ከባቢ እንዲፈጠር ለማስቻል የልማት አጋሮች ትብብር ወሳኝ ሚና ያለው በመሆኑ ነው ውይይቱ የተዘጋጀው፡፡

በኢሊሊ ሆቴል በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ የስራ አመራር ቦርድ አባል ኢንጂነር አለማየሁ ንጋቱ ምክር ቤቱ ለሚሰራቸው ስራዎች የሚደረጉ ድጋፎች የሚበረታቱ እና ውጤታማ እንደነበሩ አንስተው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡

የምክር ቤቱን ያለፉትን ዓመታት ጉዞ እና ዓላማዎች ያቀረቡት የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በተለያዩ ፕሮጀክቶች በተሰሩ ስራዎች ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቅሰው አሁን ምክር ቤቱ በሪፎርም ላይ መሆኑንና በተለያዩ ዘርፎች ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየሰራ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

ከ77 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው እና በአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ምክር ቤቱ ለአጠቃላይ የንግዱ ማህበረሰብ ድምጽ በመሆን የተሻለ ቢዝነስ እንዲሰራና ለኢኮኖሚ እድገቱ የላቀ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ለማድረግ እየሰራ ስለመሆኑም በመድረኩ አቅርበዋል፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ ጂ አይ ዜድ እና ጃይካን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የልማት አጋር ድርጅቶች በተሳተፉበት ውይይት ድርጅቶቹ አሁንም ያላቸውን ትብብር እንደሚያጠናክሩ አንስተዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia