Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Apr 28, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የገበያ ማዕከል የምርቃት  መርዐ ግብር ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ የመጀመሪያ ዙር እድሳት እንዲሁም ፤ የሕንፃው ወለልን አፍርሶ መልሶ የማልማት ፕሮጀክት መጠናቀቂያና  የገበያ ማዕከል የምርቃት  መርዐ ግብር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የአሁኑና የቀድሞ የምክር ቤቱ የዴሬክተሮች ቦርድ አባላት፤ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችን ጨምሮ ከተለያዩ  አካላት የተወጣጡ እንግዶች በተገኙበት ተካሄደ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የንግድና ቀጣናዊ  ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ ምክር ቤቱ በትውልድ ቅብብሎሽ የግሉን ዘርፍ በመወከል በርካታ ስራዎችን እየሰራ መቆየቱን ገልጸው አሁንም የተባበረ የድጋፍ ማዕከል የመሆን፣ የፖሊሲ አድቮኬሲ ሥራዎች፣ ንግድን ማዘመንና ከመንግሥት መሪነት ወደ ግል መሪነት የሚደረገውን የኢኮኖሚ ሽግግር እንዲሳለጥ የማድረግ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሕንጻ በ1957 ተመርቆ ወደስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ያለበቂ እድሳት የቆየ በመሆኑ ምክንያት ከአካባቢው የዲፕሎማሲ እና የንግድ ማዕከልነት አንጻር የሕንጻ ጥራትና ውበት እንዲሁም ለንግዱ ኅብረተሰብ የሚጠበቅበትን አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ብዙ የማሻሻያ ስራዎች የሚጠብቅ ሆኖ ቆይትዋል ያሉት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ፡-

በመሆኑም፤ ከአካባቢው የኮሪደር ልማት ጋር በማጣጣም ለአዲስ አበባ ከተማ ውበት በሚጨምር መልኩ እንዲታደስ የተደረገው  የምክር ቤቱ ዋና መስሪያ ቤት፤  ከዚህም ባሻገር  የመጀመሪያውን ወለል  የንግድ ማዕከል እንዲሆን በማመቻቸት ለንግዱ ማኅበረሰብ ምቹ አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ የማሻሻያና የእድሳት ስራ ተከናውኖለታል፡፡

የምክር ቤቱ  በተጨማሪም በቅርብ ጊዜያት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት  ምክር ቤታችንን የንግድና ኢንቨስትመንት ዲፕሎማሲ ማዕከል ፣ የውይይት፣ የትብብርና የንግድ ማከናወኛ መድረክ በማድረግ ወደ አዲስ ምዕራፍ  የማሸጋገር ጅማሯችን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በሕንፃው እንደ አዲስ የተደራጀው የንግድ ማዕከልም  የምክር ቤቱን  የውስጥ አቅም ብቻ  ለማሻሻል ተብሎ የተሰራ ሳይሆን ከአካባቢው ውበት ጋር ተዋሕዶ የከተማይቱን የንግድና ዲፕሎማሲ ማዕከልነት ለማጠናከርም ጭምር ነው።

ምክር ቤቱ  እንደ አገራዊ የግሉ ዘርፍ ተወካይነቱ ለግሉ ዘርፍ እድገት ከመንግስትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት ላይ ይገኛል። በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች በመታየት ላይ ይገኛሉ። በተለይም አዲሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ በ ተመርጦ ኃላፊነትን ከተረከበ ጀምሮ በምክር ቤቱ ዓላማዎችን ከማስፈጸም አንጻር ሰፋፊ ስራዎች ሲከናወኑ  የቆዩ መሆኑን ገልጠው የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia