Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 22, 2025 .

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ 84 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በ3ኛው የደረጃዎች ቦርድ በማስጸደቅ ወደ ተግባር አስገብቷል ::

▶️ የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ በቅርቡ ባካሄደው  3ኛ መደበኛ ስብሰባው ለሀገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ በሆኑ ብሔራዊ ደረጃዎች ላይ ሰፊ ውይይትና ምርመራ ካደረገ በኋላ ማፅደቁ  ይታወሳል።

▶️ 68 አስገዳጅ ደረጃዎችን እና 16 የፍተሻ ዘዴ/ደረጃዎችን በድምሩ 84 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በ3ኛው የደረጃዎች ቦርድ በማስጸደቅ ወደ ተግባር አስገብቷል ::

▶️ የጸደቁት ደረጃዎች በሦስት ዘርፎች የተለዩ ሲሆን

1. በኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ዘርፍ ፡

ሀ. የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶች / Natural Gas Products ብዛታቸው 9 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች ፣ለዚሁ ለፈጥሮ ጋዝ ምርቶች የሚያገለግሉ 11 የፍተሻ ደረጃዎች ጋይድላይን /Test Method standards and guidelines.

2. በኤሌክትሮ ሜካኒካል ዘርፍ፡-

ሀ. የተፈጥሮ ጋዝ መሰረተ ልማት ደረጃዎች /Natural gas Infrastructure and Facilities ብዛታቸው 23 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች ፣

ለ. የኃይል ፋክተር ማስተካከያ /power factor corrector ብዛታቸው 7 የሆኑ አዲስ አስገዳጅ ደረጃዎች፣ በዚሁ ዘርፍ ስር 5 የፍተሻ  ደረጃዎች/ Test Method Standards and guidelines.

ሐ. የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች/ Electrical House hold Appliances የማቀዝቀዣ/ፍሪጅ 1 አዲስ አስገዳጅ ደረጃ

3. በኮንስትራክሽን እና የሲቪል ምህንድስና ዘርፍ ፡-

የብረት እና አልሙኒየም/ Steel and Aluminum Structures ብዛታቸው 28 የሆኑ አስገዳጅ ደረጃዎች ናቸው::

ደረጃዎቹ ወቅታዊ የሀገሪቱን ፖሊሲ መነሻ አድርገው የተዘጋጁ እንደሆነ ታውቋል::
በተለይ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ የሚታመነው የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ገበያው በሚገባበት ጊዜ ደረጃዎቹን በመተግበር በተገቢው መንገድ ወደ ማህበረሰቡ እንዲደርስ እና ጥራቱ  የተጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል::

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia