Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Apr 22, 2025 .

የኢትዮ – ሳዑዲ የጋራ ንግድ ምክር ቤት ስብሰባ በሪያድ ተካሄደ::

የኢትዮ – ሳዑዲ   የጋራ ንግድ ምክር ቤት ስብሰባ  ተካሄደ ( ሪያድ፣ ሚያዚያ 14 ቀን 2017)

 

የኢትዮ – ሳዑዲ   የጋራ ንግድ ምክር ቤት  የመጀመሪያው ስብሰባ ተካሄደ።  ስብሰባው  በኢትዮጵያ  ወገን የንግድ  ም/ቤቱ ሊቀመንበር ዶ/ር  ሃሰን አብዱላሂ  እና በሳዑዲ ወገን  የጋራ ም/ቤቱ ሊቀመንበር Mr. Abdullah Alajmi በጋራ የተመራ  ሲሆን  በውይይቱም በሁለቱ አገራት ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በማውሳት  ይህንንም  በኢኮኖሚው ዘርፍ ማጠናከር   እንደሚገባ ተገልጿል።

መድረኩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ትስስር የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን አዲስ የኢኮኖሚ ትብብር እና የስትራቴጂክ አጋርነት ምዕራፍ የሚያመጣ እንደሆነ በውይይቱ ተነስቷል።

በስብሰባው የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር እንዲያስችል በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ  በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ፣ በግብርና፣ በማዕድን ፣ በቱሪዝም እና በኮንስትራክሽን ዘርፎች አብሮ ለመስራት ተስማምቷል።( በሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia