Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብዱልሀኪም ሙሉ እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት  ሰብስብ አባፊራ  አባጆቢር ናቸው፡፡

በሀይሌ ግራንድ ሆቴል  በተካሄደውን የስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት ከሁለቱ መስሪያ ቤቶች ባለፈየቦርድ አ ባላት፤ የክልል የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ሁለቱ አካላት ስምምነቱን የተፈራረሙት በተለይም በመንግስትና በግል ዘርፉ የሚካሄዱ የምክክር ስራዎችን ለማጠናከር በሚቻልበት የኤሌክትሮኒክ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ምክክር ዙሪያ ነው፡፡

በስምምነት ስነ ስርዓቱም ሀገራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል መተባበርና አብሮ መስራት እንደሚጠበቅና መንግስትም የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ እየሰራ መሆኑን ተነስቷል፡፡

የምክክር መድረኮችም ተጠናክረው መቀጠል እንደሚጠበቅባቸውና በአብሮነትና በጋራ አብሮ ለመስራት ኤሌክትሮኒክ የግሉ ዘርፍና የመንግስት ምክክር መድረክ አስፈላጊ በመሆኑ ሁለቱ ተቋማት በትብብር እንደሚሰሩም በስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia