Jan 22, 2026 .
የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የስድስት ወራት የንግድ ዘርፍ አፈጻጸም የሴክተር ጉባኤያችንን በደሴ ከተማ በስኬት አጠናቀናል:- ካሳሁን ጎፌ(ዶክተር)


የኢፌድሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የስድስት ወራት የንግድ ዘርፍ አፈጻጸም የሴክተር ጉባኤያችንን በደሴ ከተማ በስኬት አጠናቀናል።
የዘንድሮው የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ለንግድ ዘርፍ እድገት ወሳኝ ሚና በተጫወቱ በርካታ ሃገራዊ እመርታዎች የታጀበ ነው።
በሚኒስቴር መስሪያቤታችን በስትራቴጂካዊ ሃሳቦች በተመራ በስካሁኑ የተቋም ግንባታ ሪፎርማችን የስኬቶቻችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውነናል።

በሃገር ወስጥ ንግድ፣ በወጪ ንግድ ግኝት፣ በንግድ ትስስር፣ በጥራት ማረጋገጥና የዲጂታል ንግድ ያስመዘገብናቸው አመርቂ ውጤቶች በፍጥነት፣ በፈጠራና በልህቀት የታጀበው ሃገራዊ የብልጽግና ጉዞአችንና የኢኮኖሚ ሪፎርማችን በትክክለኛ የዕድገት መንገደ ላይ ስለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ናቸው።
በቀጣይም የኢትዮጵያን ዐቅሞች ይበልጥ በመግለጥ የንግድ ዘርፉን ዘመኑን የዋጀ፣ ዛሬን ተወዳዳሪና ነገን ተሻጋሪ እንዲሆን ለማስቻል በመሰጠት፣ በመቀናጀትና በማላቅ ቁልፍ እሴቶቻችን ተመርተን በቁርጠኝነት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
ካሳሁን ጎፌ(ዶክተር)
የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር

