Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

May 21, 2025 .

የ2026 የዛይድ የዘላቂ መፍትሄ ሽልማት (2026 Zayed Sustainability Prize) ውድድር

       

የ2026 የዛይድ የዘላቂ መፍትሄ ሽልማት (2026 Zayed Sustainability Prize) ውድድር እድል
ለንግዱ ማኅበረሰብ ፣ ለአጋር አካላት እና የሚመለከታችሁ ሁሉ!
የዛይድ የዘላቂ መፍትሄ ሽልማት (Zayed Sustainability Prize) በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መስራች አባት ተደርገው በሚቆጠሩት ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን ስም የተቋቋመውና በየዓመቱ በተመረጡ ዘርፎች ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ለሚያቀረቡ ስራ ፈጣሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ባለሙያዎች የቀረበ የፕሮጀክት ውድድር ነው፡፡
የ
2026 የዛይድ የዘላቂ መፍትሄ ሽልማት (2026 Zayed Sustainability Prize) ለአሸናፊ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 5.9 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡ የሚቀርቡ ፕሮጀክቶችም፡
❇️ በጤና
❇️በምግብ
❇️በኃይል አቅርቦት
❇️በውኃ እንዲሁም
❇️በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች የተሻለ የምርምር ውጤት እና ችግር ፈች መፍትሄ ላላቸው አሸናፊዎች ፕሮጀክቶች ለእያንዳንዳቸው የ1 ሚሊየን ዶላር ሽልማት ተመድቧል፡፡
❇️በሌላ በኩል ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 150 ሺ ዶላር በሽልማት መልክ ተዘጋጅቷል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት ዘርፎች ላይ
❇️በፈጠራ ፕሮጀክት፣ በምርምር ውጤት ወይም በተጠቀሱት ዘርፎች እየሰራችሁ ያላችሁ እና ለመወዳደር የምትፈልጉ አካላት፣
❇️አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣
❇️ በዘርፉ የምትሰሩ ተቋማት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች
❇️በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ ተማሪዎቻችሁን በማሳተፍ የምትሰሩ ትምህርት ቤቶች ከታች በተጠቀሰው አድራሻ እንድታመለክቱ ጥሪ ቀርቦላችኋል፡፡
o   ማመልከቻ አድራሻ-  www.ZayedSustainabilityPrize.com
o   ለማንኛውም ጥያቄ –Ali Yasir– ayasir@masdar.ae  ይጻፉ
o   የማመልከቻ ቀን እስከ ሰኔ 16/2017 ዓ.ም ብቻ
ማሳሰቢያ፡-
የሚቀርቡት ፕሮጀክቶች ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘላቂ የልማት ግቦች ጋር የተያያዙ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
o   ሽልማቱ ከዚህ በፊት- በ150 ሀገራት ለ128 ፕሮጀክቶች ሽልማት ሰጥቷል
o   ፕሮጀክቶቹ ከ400 ሚሊየን በላይ ህዝብ ላይ ተጽእኖ መፍጠር ችለዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia