Feb 17, 2026 .
ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከአለም ባንክ ከመጡ የተለያዩ የስራ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋርመክረዋል።



የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ከአለም ባንክ ከመጡ የተለያዩ የስራ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ባንኩ በቅርቡ ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዉን ባጠናቀቀዉ ቡስቲንግ የተሰኘዉን ፕሮጀክት በጋራ ለመተግበር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።
ፕሮጀክቱ የሚያተኩርባቸዉ ዋና ዋና ነጥቦች የንግድ መዳረሻዎችን ለማስፋት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ የኢትዮጵያ ላኪዎችን የዉጭ ምንዛሪ ችግር ሊፈታ የሚችል ንግድን ፋይናንስ ማድረግና ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር ላይ መሆኑ በዉይይቱ ተነስቷል።

የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የአለም ባንክ ተግባራዊ ለማድረግ የቀረፀዉ ፕሮጀክት የትኩረት አቅጣጫዎች ከምክር ቤቱ ዋና ዋና ተልዕኮዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸዉ እንደመሆናቸዉ መጠን ከባንኩ ጋር በመስራት ንግድና ኢንቨስትመንትና በማስፋፋትና የንግድ መዳረሻዎችን በማስፋት ቀጣናዊ ትስስሩን የማጠናከር ስራ ለመስራት ምክር ቤቱ ከምንጊዜዉም የተሻለ አቅምና ዝግጁነት እንዳለዉ አረጋግጠዋል።

