Oct 05, 2026 .
ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው መስራች ጉባኤ ክቡር የትምጌታ አስራትን (ዶ/ር) የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በመሰየሙ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው መስራች ጉባኤ ክቡር የትምጌታ አስራትን (ዶ/ር) የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በመሰየሙ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ፕሬዚደንቱ በመልዕክታቸው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በታታሪ የሰው ኃይል፣ በምርታማ መሬት፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እድሎች የታደለ ክልል ነው። ይህን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሥራ ዕድል፣ የምርታማነት እና የንግድ ማስፋፊያ ለመቀየር የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ቅንጅት ወሳኝ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ አዲስ አመራር ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት በመሥራት የኢንቨስትመንትና የንግድ አካባቢን የበለጠ እንደሚያሻሽል ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
አክለውም ፤ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትም የግሉ ዘርፍን በማስተባበርና በመወከል ለክልሉ የኢኮኖሚ እና የንግድ ልማት አጋርነቱን ለማጠናከር ዝግጁ ነው።
ለዶ/ር የትምጌታ አስራት እና ለመላው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ሰላም፣ ስኬትና የተሻለ የልማት ጉዞ እመኛለሁ ብለዋል።

