Feb 05, 2026 .
15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት በመስቀል አደባባይ ተከፈተ።

15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት በመስቀል አደባባይ ተከፈተ።
በኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀው 15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም ዓቀፍ የንግድ ትርኢት ከጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መስቀል አደባባይ መካሄድ ጀምሯል።
የንግድ ትርኢቱ ቁልፍ ዓላማዎች
ይህ ዓመታዊ መድረክ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን ያለመ ሲሆን፣ በዋናነት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ያተኩራል፦
* የሀገር ውስጥ ምርትን ማስተዋወቅ፦ የኢትዮጵያን ምርቶች፣ አገልግሎቶችና ጥሬ ዕቃዎች ለዓለም ገበያ ማሳየት።
* የቴክኖሎጂ ሽግግር፦ ለኢንዱስትሪ ልማትና ለሥራ ፈጠራ የሚያግዙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ።
* የገበያ ትስስር፦ በሀገር ውስጥና በውጭ ኩባንያዎች መካከል የ”አቻ ለአቻ” (B2B) የንግድ ውይይቶችን ማመቻቸት።
በዘንድሮው የንግድ ትርኢት ላይ የሚሳተፉት አካላት ስብጥር ሰፊ ሲሆን፦
* ከ20 በላይ ሀገራት የተውጣጡ፤
* ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች፤
* ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ ድርጅቶች
ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው ቀርበዋል።
የንንግድ ትርኢቱ ለሁሉም ጎብኚዎች ክፍትት ነዉዉዉ። ይዮጎብኙ፣የሚያሻዎትን ይሸምቱ።

