May 29, 2025 .
የሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ጋር በልምድ ልውውጥ መድረክ ዙሪያ ተወያዩ፡፡



የሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 23 ቀን 2017 የሚያካሂደውን የልምድ ልውውጥ መድረክ በማስመልከት ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ጋር ተወያየ።
የሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት መጋቢ ስርዓት ቄሲስ ታዬ ለታ በጋራ የውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት ፤ ምንም እንኳን መርሐ ግብሩ የሚዘጋጀው በሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ቢሆንም ለፕሮግራሙ ስኬት የኢትዮጵየ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ትብብርና እገዛ ወሳኝ ነው።



የኢትዮጵያ ን/ዘ/መ/ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) በበኩላቸው የሸገር ን/ዘ/ማ/ም/ቤት ከተመሰረት አጭር ጊዜ ቢሆንም ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ስራዎች ይበል የሚያሰኙና ሊበረታቱ የሚገቡ መሆናቸውን አንስተው ም/ቤቱ ላከናወናቸው ተግባራት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።
የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብሩን ለማሳካት አስፈለጊውን ተቋማዊ እገዛ ከማድረግ ባሻገር ለሁለንተናዊ ስኬቱ የኢ/ን/ዘ/ማ/ም/ቤት ምንጊዜም እገዛው እንደማይለያቸውም አረጋግጠዋል።


