Jul 18, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የሥራ ኃላፊዎች መቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማኀበርን ጎበኙ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የሥራ ኃላፊዎች መቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማኀበርን ጎበኙ።
የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሣ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሠር) እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ናቸው ማኀበሩን የጎበኙት። ምክር ቤቱም ለበጎ አድራጎት ማኀበሩ የግማሽ ሚሊየን ብር የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
ምክር ቤቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደ መቄዶኒያ ካሉ በጎ አድራጎት ተቋማት ጋር በትብብር የሚሠራ ምክር ቤት መሆኑን የገለጹት ዶክተር ቀነኒሣ በቀጣይም ለማኀበሩ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
የንግዱ ማኀበረሠብ ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኀበር የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር የማኀበሩ መሥራች ክቡር ዶክተር ቢኒያም በለጠ አሣሥበዋል።


