Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com
Latest News
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባል ምክር ቤቶችን ተቋማዊ አቅም እንዲሁም የአሠራር ብቃትን ለማጠናከር የጀመረውን የአቅም ግንባታ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እያከናወነ ነው። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በተካሄደው 8ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ ተገለጸ። በንግድ ዘላቂነት እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት ስትራቴጂካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቋል። የካፒታል ጋዜጣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ሰፊ፣ዝርዝርና ሙያዊ ቆይታ አድርጓል። በተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራውና የምክር ቤቱን የቦርድ አባላት ያካተተው ልዑክ፣ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በኤግዚቢሽኑ ተሳትፏል። ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ማኅበረሰብ ጋር ማገናኘት የውጭ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉብኝቶቻችን ዋነኛ ዓላማ ነው።

Read more

May 14, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከመንግስት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከልማት አጋሮች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ንቁ የግል ዘርፍ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከመንግስት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከልማት አጋሮች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ንቁ የግል ዘርፍ እና ለንግድ ተስማሚ አካባቢን በመፍጠር ንግድ እና ኢንቨስትመንትን የማሳደግ፣ የአቅም ግንባታ ድጋፍ  የመስጠት እና የምርምርና የአድቮኬሲ ሥራዎችን የማከናወን ኃላፊነት አለበት።

ሀገራዊ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቱ

❇️ የንግድ ማህበረሰቡን በንግድና ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ኩነቶችና ትእይንቶች ላይ ያሳትፋል፣የንግድ ትርኢቶች/ኤግዚቢሽን ያዘጋጃል፣

❇️ ሕግ ማማከር እና የግልግል ዳኝነት ይሰጣል

❇️ የንግድ ማውጫ ያዘጋጃል፣ ወቅታዊ የንግድ መረጃዎችን ለንግዱ ማህበረሰብ ይሰጣል፣

❇️ የአባላትን ተጨባጭ ተሞክሮዎች ያጋራል፣ድጋፍ ይሠጣል፣

❇️  ምክር ቤቱ የንግድ ግንኙነቶችን በመፍጠርና ያሉትንም በማጠናከር በዓለም አቀፍ የገበያ ስርዓት ውስጥ እውቅናን
እንዲያገኙ ያግዛል፣ ማህበራዊ ኃላፊነትን ያጠናክራል፣

❇️ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ሥራዎች ይሠራል፣ መመሪያዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣

❇️ የአምራች አገር የምስክር ወረቀት ማረጋገጫ  እንዲሁም የሰነድ ማረጋገጫ (የላኪዎች) አገልግሎት ይሠጣል፣

❇️ የንግድ ድጋፍ አገልግሎት ይሰጣል፣

❇️ ምክር ቤቱ የንግድ ሥራ ክህሎት በማሳደግ ከሌሎች የንግድ መሪዎች እና ከንግድ ማህበረሰቡ ጋር እንዲገናኙ ዕድሎችን ያመቻቻል፤

❇️ የቴክኒክ እና የክህሎት ስልጠናዎችን ያመቻቻል፣በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ሥልጠና ይሠጣል፣ የንግድ ትምህርት ሴሚናሮችን ያዘጋጃል፣

❇️ የምርምር እና አድቮኬሲ ሥራዎች ይሠራል፣ የተለያዩ ህትመቶች ያወጣል፣

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia