Feb 09, 2026 .
ከጥር 27 – የካቲት 01 ቀን 2018 ዓ.ም እየተካሄደ የሚገኘው 15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ ።




የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከጥር 27 – የካቲት 01 ቀን 2018 ዓ.ም እየተካሄደ የሚገኘው 15ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ ።
በመርሐ ግብሩ ላይም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢርና የቦርድ አባላት፣የምክር ቤቱ ዋና ፀኃፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተወካዮች፣ የኩባንያዎች ባለቤቶችና ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡



