Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 11, 2026 .

በንግድ ምክር ቤት ሥርዓት ውስጥ የንግድ ዘላቂነት (Business Sustainability in the Chamber System) እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ነዉ።

  

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለአባል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ዋና ፀሐፊዎችና የአባላት ጉዳይ ዳይሬክተሮች በንግድ ምክር ቤት ሥርዓት ውስጥ የንግድ ዘላቂነት (Business Sustainability in the Chamber System) እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት (Membership Database System)” በሚሉ ሁለት ዋና ዋና እና ስትራቴጂካዊ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቢሾፍቱ ከተማ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ነዉ።

የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ ስልጠናዉን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ስልጠናዉ በተቋማችን ሁለንተናዊ እድገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለዉ ብለዋል።

አክለዉም የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤታችን የግሉን ዘርፍ ድምፅ የማሰማት፣ የንግድና ኢንቨስትመንት አካባቢን የማሻሻል እና የአባላቱን መብትና ጥቅም የማስጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነቱን ለመወጣት ጠንካራ፣ ዘመናዊና በራሱ አቅም መቆም የሚችል የንግድ ምክር ቤት ሥርዓት (Chamber System) መገንባት ግድ እንደሚልም ገልፀዋል።

በመሆኑም የንግድ ምክር ቤታችን ዘላቂነት (Business Sustainability) የሚረጋገጠው ተቋሞቻችን የፋይናንስ፣ የአሰራር እና አገልግሎት የመስጠት አቅማቸውን ማሳደግ ሲችሉና ለውጦችን የሚቋቋም ጠንካራ መዋቅር ሲኖራቸው ነዉ ያሉት ዋና ፀሐፊዋ፣ ይህ ደግሞ እዉን ሊሆን የሚችለዉ በዋናነት በየደረጃው በሚገኙ አባል ምክር ቤቶቻችን አመራሮች የአመራር ብቃትና እና ቁርጠኝነት ነው ብለዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia