Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 12, 2026 .

ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ማኅበረሰብ ጋር ማገናኘት የውጭ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉብኝቶቻችን ዋነኛ ዓላማ ነው።

ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ማኅበረሰብ ጋር ማገናኘት፣ የግሉን ዘርፍ ተወዳዳሪነት ማሳደግ፣ የኢትዮጵያን ምርቶችና አገልግሎቶች ማስተዋወቅ እንዲሁም አዳዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎችን መፍጠር የውጭ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉብኝቶቻችን ዋነኛ ዓላማ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች በጣሊያን እያደረግን ባለነው የንግድ እና የኢንቨስትመንት ጉብኝትም እነዚህን ዓላማዎች ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያግዙ ጠቃሚ እድሎችን እያገኘንበት ነው።

በዓለም አቀፍ የግብርና ማሽነሪዎች ኤግዚቢሽን እያደረግነው ባለው በዚህ ተሳትፎ የጣሊያንን የላቀ የቴክኖሎጂና የማሽነሪ ልምድ ለመቅሰም፣ ከዓለም አቀፍ አምራቾችና አቅራቢዎች ጋር ለመገናኘት፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኩባንያዎች አዳዲስ የንግድና የሽርክና እድሎችን ለመፍጠር እያስቻለ ያለ መድረክ ሆኖልናል።

በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያና በጣሊያን ኩባንያዎች መካከል የቢዝነስ ለቢዝነስ (B2B) ግንኙነቶችን ማጠናከር አንኳር ተግባር ሲሆን- በዚህ መነሻም የተፈጠሩ የንግድ ግንኙነቶቹ ወደ ተጨባጭ የንግድ ስምምነቶች፣ የጋራ ኢንቨስትመንቶች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ዘላቂ የኢኮኖሚ ትብብር እንዲያድጉ ጠንካራ መሠረት ይፈጥራሉ።

ከዚህም ባሻገር ፤ በተለይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከኢትዮጵያ ገበያ የወጡ የጣሊያን ኩባንያዎች እንደገና ወደ አገራችን በመመለስ ያሉትን የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲጠቀሙ ለማበረታታት በሮም የኢፌዴሪ ኤምባሲ ጋር በመሆን የምናደርገው ጥረት የጉብኝቱ አንዱ የትኩረት መስክ ነው።

በዚህ ረገድ በሮም የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተጠባባቂ ጉዳይ ፈጻሚ አስተባባሪነት ፤አቶ አንዳወቀ ተስፋዬን ጨምሮ የኢኮኖሚ አታሼ እስክንድር ተሾመ እና በየደረጃው የሚገኙ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች በሁለቱ አገራት ኩባንያዎች መካከል የB2B ግንኙነቶች እንዲፈጠሩና ከላይ በጠቀስኩት አግባብ ውጤት እንዲያስገኙ እያደረጉት ስላለው ከፍተኛ ጥረት ፤ እንዲሁም ለተሳትፎዋችን ስኬትና ለሁለቱ አገራት የንግድ ማኅበረሰቦች መቀራረብ እያከናወኑት ላለው አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia