ቡና የኢትዮጵያ ታሪካዊ መለያ፣ የባህላችን አካል እና የኢኮኖሚያችን ምሰሶ ነው።

ቡና የኢትዮጵያ ታሪካዊ መለያ፣ የባህላችን አካል እና የኢኮኖሚያችን ምሰሶ ነው። ከባህላዊ እሴቱ ባሻገር ግን ለሚሊዮኖች ዜጎቻችን የኑሮ መሠረት እንዲሁም ለሀገራችን ደግሞ ከዋነኞቹ የውጭ ምንዛሬ ምንጮች አንዱ ነው።
በዚህ መነሻ ፤ በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው የዓለም የቡና ኤግዚቢሽን 2026 እንዲሁም ነገ በጅማ ከተማ የሚካሄደው WORLD COFFEE RUN 2026፤ የቡና ምርታችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የገበያ ትስስርን ለማጠናከር እና የሀገራችንን የቡና ቅርስና ኢኮኖሚያዊ አቅም ለዓለም ለማሳየት ወሳኝ አጋጣሚዎች ናቸው።
የቡና ዘርፉ ያለውን አሁናዊ የኢኮኖሚ ፋይዳም ሆነ አቅም ወደ ተሻለ ኢኮኖሚያዊ ውጤት ለመቀየር የቡና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ ጥራትን ማረጋገጥ፣ የአቀራረብና የማቀነባበር ሥርዓትን ማዘመን፣ በዓለም ገበያ ያለንን ተወዳዳሪነት ማጠናከር እና የቡና ምርቶችን በተጨማሪ እሴት ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይጠይቃል።
ይህም፤ በመንግሥት ተቋማት፣ በቡና አምራቾች፣ በኤክስፖርተሮች፣ በባለሀብቶች፣ በማኅበራትና የሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች የተቀናጀ ትብብርን ይሻል።
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትም ሆነ የዚህ ዝግጅት ዋንኛ አዘጋጅ የሆነው የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ የመወከል፣ የንግድ ትስስርን የማሳደግ፣ የገበያ እድሎችን የማስፋትና የግሉ ዘርፍ ተወዳዳሪነትን የማጠናከር ሚናውን በመወጣት ለቡና ዘርፉ ዕድገት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል።
WORLD COFFEE RUN 2026 ደግሞ ስፖርትን ከቡና ባህል፣ ከቱሪዝምና ከኢኮኖሚያዊ እድሎች ጋር የሚያገናኝ ትርጉም ያለው መድረክ ነው።
ይህ ዓይነቱ ተሳትፎ የአካባቢውን የቡና ሀብት በማስተዋወቅ የቱሪዝም እንቅስቃሴን፣ የንግድ ግንኙነትንና ኢንቨስትመንትን ለማነቃቃት የራሱን ሚና ይጫወታል።
በመሆኑም፤ በኦሮሚያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት በየአመቱ የሚካሄደው ይህ መርሐ-ግብር በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል።
በመጨረሻም፤ የዓለም የቡና ኤግዚቢሽን 2026 አዘጋጆችን፣ ተሳታፊዎችን፣ የቡና አምራቾችን፣ ነጋዴዎችንና አጋር ተቋማትን እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።
በነገው WORLD COFFEE RUN 2026 ላይ ለሚሳተፉ ሁሉ መልካም የስፖርት ተሳትፎና ስኬት እመኛለሁ።
የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያና ኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ፕሬዚዳንት
Coffee is Ethiopia’s historic identity, an integral part of our culture, and a pillar of our economy. Beyond its cultural significance, coffee is a source of livelihood for millions of our citizens and one of the country’s major sources of foreign exchange earnings.
In this context, the World Coffee Exhibition 2026, currently taking place in southwestern Oromia, and the WORLD COFFEE RUN 2026, scheduled to take place tomorrow in Jimma, present important opportunities to promote Ethiopian coffee internationally, strengthen market linkages, and showcase our country’s rich coffee heritage and economic potential to the world.
To translate the coffee sector’s current economic significance and potential into greater economic gains, we must increase coffee production and productivity, ensure quality, modernise processing and presentation systems, strengthen our competitiveness in the global market, and promote value addition to coffee products before exporting them.
Achieving these objectives requires coordinated efforts and strong collaboration among government institutions, coffee producers, exporters, investors, business associations, and other stakeholders across the sector.
Both the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations and the Oromia Chamber of Commerce and Sectoral Associations, the principal organiser of this event, have important roles to play in representing the private sector, strengthening business linkages, expanding market opportunities, and enhancing private-sector competitiveness. They are expected to further strengthen their contributions to the growth and development of the coffee sector.
WORLD COFFEE RUN 2026 is also a meaningful platform that brings together sport, coffee culture, tourism, and economic opportunities.
This initiative plays an important role in promoting the region’s coffee resources, stimulating tourism, strengthening business relationships, and encouraging investment.
Furthermore, this annual event, organised by the Oromia Chamber of Commerce and Sectoral Associations, will continue in the coming years with renewed strength and an enhanced scope.
Finally, I would like to extend my congratulations to the organisers of the World Coffee Exhibition 2026, participants, coffee producers, traders, and partner institutions for their contributions to this important event.
I wish all participants in tomorrow’s WORLD COFFEE RUN 2026 a successful and memorable sporting experience.
H.E. Sebsib Abafira Abajobir
President of the Ethiopian and Oromia Chambers of Commerce and Sectoral Associations.

