Nov 15, 2026 .
በጅማ ከተማ የተካሄደው የቡና ሩጫ እና አለማቀፍ የቡና ኤግዚቢሽን በቀጣይም በየዓመቱ አለማቀፋዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል- የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ

በኦሮሚያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና በጆርካ ኢቨንት በጅማ የተዘጋጀው የታላቁ የመንገድ ላይ ውድድር ዝግጅት ውብ በሆነ ድባብ ተካሂዷል።
በሁለቱም ጾታዎች ሰፊው የጅማና አካባቢው ማህበረሰብን ጨምሮ ከመላው ኢትዮጵያ የተሰባሰቡ አትሌቶች ተሳትፈዋል።
ከአንደኛ ደረጃ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ለወጡት አሸናፊዎች ለሁለቱም ጾታዎች
▶️ 1ኛ አሸናፊ 500,000 ብር፣
▶️ ሁለተኛ ደረጃ አሸናፊዎች 200,000 ብር እና
▶️ ሶስተኛ ደረጃ አሸናፊዎች 150,000 ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

ይህ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት እና በጆርካ አስተባባሪነት በጅማ ከተማ የተካሄደው የቡና ሩጫ እና አለማቀፍ የቡና ኤግዚቢሽን በቀጣይም በየዓመቱ አለማቀፋዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያና ኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ፕሬዚዳንት

