የዓለም ቡና ቀንን አስመልክቶ የተሰናዳው WORLD COFFEE RUN 2026 የጎዳና ላይ ሩጫ በጅማ ከተማ ተካሄደ።


የዓለም ቡና ቀንን አስመልክቶ የተሰናዳው WORLD COFFEE RUN 2026 የጎዳና ላይ ሩጫ በጅማ ከተማ ተካሄደ።
የኢትዮጵያና ኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ፕሬዚዳንት የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር እንደገለፁት ፤ ይህ የጎዳና ላይ ሩጫ ስፖርትን ከቡና ባህል፣ ከቱሪዝምና ከኢኮኖሚያዊ እድሎች ጋር የሚያገናኝ ልዩ መድረክ ነው። ይህ ዝግጅት ሰዎችን ለጤናማ አኗኗርና ለስፖርት ተሳትፎ ከማነሳሳቱ በተጨማሪ፣ የጅማንና የአካባቢውን የቡና ሀብት ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ለማስተዋወቅ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
ጅማ የቡና ታሪክና ቅርስ የሚገለጽባት ከተማ ናት። ስለዚህ ይህንን መሰል ዝግጅት በጅማ መካሄዱ የከተማዋን ስም ከቡና ባህል ጋር በማገናኘት የቱሪዝም፣ የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋት የሚያግዝ ነው።

ፕሬዚደንቱ አክለውም ፤ ይህ ዓመታዊ መርሐ ግብር በኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል፣ ይበልጥ ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎን እንዲያጎለብትና ተጨባጭ የንግድ ውጤቶችን እንዲያመጣ የተቻለንን ጥረት ሁሉ የምናደርግ ይሆናል ብለዋል።
በውድድሩ አትሌቶችና ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል።
በሁለቱም ጾታዎች ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለወጡ ተወዳዳሪዎችም ሽልማት ተበርክቷል።
ውድድሩን ያዘጋጀው የኦሮሚያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ነው።

