Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

May 30, 2025 .

Breakthrough Trading አክሲዮን ማኀበር በቀጥታ ሽያጭ ( Direct Selling) ላይ ባካሄደው ጥናት ዙሪያ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር ተወያዬ።

Breakthrough Trading አክሲዮን ማኀበር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን በቀጥታ ሽያጭ ( Direct Selling) ላይ ባካሄደው ጥናት ዙሪያ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር ተወያዬ።

በቀጥታ ሽያጭ (Direct Selling) ዙሪያ ከሌሎች ተመሣሣይ ሀገራት ጋር ያለውን ተሞክሮ እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመቃኘት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ሊያመጣ የሚችለው ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ተጽእኖ በተመለከተ “The Social and Economic Impact of Direct Selling in Ethiopia and its Legal Grounds” በሚለው ጥናት በስፋት ተዳሷል።

የቀጥታ ሽያጭ በኢትዮጵያ ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ እንደሚያሥፈልገው የገለጹት ጥናቱ አቅራቢዎቹ ይህም ለተጠቃሚውም፣ ለአምራቹም ሆነ ሻጩ ትክክለኛ ግብይት እንዲኖር ያሥችላል ብለዋል።

በዚህ ሂደት በቀጥታ ሽያጭ የሚያደርጉ ተቋማት ሥትራቴጂ እና ራእይ እንዲሁም ግልጽ እሴት ሊኖራቸው እንደሚገባ፣ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ማውጣት እንዳለባቸው፣ የኮሚሽን  ሠራተኞችን የሚቀጥሩ ተቋማት የኮሚሽን እቅድ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልጋቸው  እንዲሁም የሽያጭ ሥነ ምግባርን በአግባቡ መከታተል እንደሚገባ ተጠቅሷል።

የምርትና አገልግሎትን በጥራትና በመጠን በትክክል ለማቅረብ፣ የተጠቃሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ያለ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት ከገዥው ወደ ተጠቃሚው በተመጣጣኝ ዋጋ ለማድረስ የቀጥታ ሽያጭ ሊበረታታ የሚገባው አካሄድ መሆኑም ተጠቁሟል።
ለዚህ ደግሞ የፖሊሲ ምእቀፍ ሊኖር እንደሚገባ እና ትኩረት የሚሻ ሥለመሆኑም ነው የተጠቆመው።

Breakthrough Trading በጉዳዩ ዙሪያ የግንዛቤ ማሥጨበጫ ሥራዎችን በስፋት ለመሥራት እንዲሁም የፖሊሲ ብሪፊንግ ሥራዎችም በመሥራት፤ ይህም በምክር ቤቱ በኩል ለሚመለከተው የመንግሥት መሥሪያ ቤት እንዲቀርብ ፍላጎት መኖሩ ተጠቅሷል።

በሌሎች ሀገራት ከተለመደው የግብይት ሥርዓት በተሻለ መልኩ የቀጥታ ሽያጭ የቁጥጥር ማእቀፍ (Direct Selling Regulatory Framework)  መኖሩን በማንሣት በኢትዮጵያም በተመሣሣይ አሠራሩም ሆነ ህጉ መኖር እንዳለበት ነው የተብራራው።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia