Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 03, 2025 .

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ ጀምሯል።

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ ጀምሯል።

በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ የሱፍ፣ የሀገራትና የዓለም አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ከጳጉሜን 3 እስከ 5/2017 ዓ.ም የአፍሪካና ሌሎች ሀገራት መሪዎች የዓለም አቀፍ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ከዚህ ጉባኤ አስቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት ያዘጋጀው 2ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ሳምንት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 1/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ ይገኛል።


የአየር ንብረት ሳምንቱ “ውይይቶችን ወደ ተግባርና ውጤት መቀየር” በሚል  መሪ ሀሳብ የአየር ንብረት ለውጥ ቃል ኪዳኖችን ወደ ሚጨበጥ የተግባር ውጤት መቀየር ላይ ትኩረቱን አድርጓል።

የሀገራትን የልማት ትልሞችና የፖለቲካ ቁርጠኝነት ወደ ተጨበጠ ጠንካራ የለውጥ እርምጃ በማቅረብ ለ2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ የፖሊሲ ሀሳቦች የሚዘጋጁበት ነው ተብሏል።

በብራዚል ለሚካሄደው 30ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ-30) የጋራ አጀንዳን ለመቅረጽ እንደሚያግዝም ይጠበቃል።

በሳምንቱ የሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምክክር፣ የጎንዮሽ ውይይት፣ የልምድ ልውውጦች፣ አውደ ርዕይና የትስስር ማጠናከሪያ መድረኮች የሚካሄዱ ይሆናል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመጀመሪያው የአየር ንብረት ሳምንት እ.አ.አ ግንቦት 2025 በፓናማ መካሄዱ ይታወሳል።(ምንጭ ኢዜአ)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia