Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 17, 2025 .

ሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቢዝነስ የአሠልጣኞች ስልጠና (Training of Trainers) ተጠናቀቀ።

ሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቢዝነስ የአሠልጣኞች ስልጠና (Training of Trainers) ተጠናቀቀ።

ስልጠናው ምክር ቤቱ ከSNV – LIWAY ፕሮጀክት እንዲሁም ከስራና ክህሎት ሚኑስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂን ውጤታማ ለማድረግና የቢዝነስ ተቋማትን አቅም ለመገንባት ያለመ ነው።



በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ የኢንፎርሜሽንና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ዋቅጅራ የምክር ቤቱ አንዱ ተልዕኮ ሥልጠናና አቅም ግንባታ መሆኑን በመጠቆም ከትምህርት ተቋማትና ከኢንዱሥትሪው የተውጣጡ ሠፊ እውቀትና ልምድ ያላቸው አሠልጣኞች ለቢዝነስ ከባቢው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።



የኢትዮጵያ ቢዝነሶች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪና ዘመናዊ አሠራርን የተከተሉ እንዲሆኑ ሥልጠናው አቅም የሚፈጥር እንደሆነም በሥልጠናው ላይ ተገልጿል።

ሥልጠናውን ላጠናቀቁ አሠልጣኞችም ከምክር ቤቱ የማጠናቀቁያ ምሥክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia