Oct 17, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከፓኪስታን የንግድና ኢንዱሥትሪ ምክር ቤቶች ፌደሬሽን ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከፓኪስታን የንግድና ኢንዱሥትሪ ምክር ቤቶች ፌደሬሽን ጋር የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ።
ሥምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨሥትመንት ትብብር ከማጠናከር ባሻገር ተቋማዊ ግንኙነትን ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሣድገው ይጠበቃል።
የመግባቢያ ሥምምነቱን የተፈራረሙት የምክር ቤቱን ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፍራ አባጆብርን በመወከል የንግድና ኢንቨሥትመንት ማሥፋፊያ ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ቃሲም እና የፓኪሥታ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤቶች ፌዴሬሽን ሲንየር ምክትል ፕሬዚደንት ሳቁብ ፋያዝ ማጉን ናቸው።

የፓኪስታን የንግድና ልማት ጉባኤ እና የሜድ ኢን ፓኪስታን ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
ሥምምነቱም የዚሁ ዝግጅት አካል ሲሆን የፓኪሥታን የንግድና ኢንዱሥትሪ ምክር ቤቶች ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ባለፈ ከፓን አፍሪካን ቻምበር ኦፍ ኮሜርስና ከሌሎች ተቋማት ጋርም የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራርሟል።

