ለሀገራችን ንግድ ማኅበረሰብ በሙሉ በየኢትዮ-አዛርባጃን የቢዝነስ ፎረም ላይ እንድትሳተፉ ስለመጋበዝ

ለሀገራችን ንግድ ማኅበረሰብ በሙሉ በየኢትዮ-አዛርባጃን የቢዝነስ ፎረም ላይ እንድትሳተፉ ስለመጋበዝ
የአዛርባጃን የንግድ ልዑካን ከኖቨምበር 24-26 ኢትዮጵያን እንደሚጎብኙ እና ከኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ በተለይም
• Construction and building materials
• Pharmaceuticals and medical supplies
• Food and beverages
• Logistics and transportation
ላይ ከተሰማሩት የሀገራችን ኩባኒያዎች እና የንግድ ተቋማት ጋር የቢዝነስ ፎረም ለማካሄድ እና አብሮ በትብብር ለመስራት ማቀዱን በመግለጽ በፎረሙ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸዉን ከላይ በተገለጹ የንግድ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ኩባኒያዎች እና የንግድ ተቋማት እንድናሳትፍ በኢሜል በላኩልን መልዕክት ትብብር ጠይቀዉናል፡፡
በመሆኑም በዚህ የኢትዮ-አዛርባጃን የቢዝነስ ፎረም ላይ በመሳተፍ ያለዉን እድል ለመጠቀም ፍላጎት ያላችሁ የሀገራችን የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት እስከ ኖቨምበር 19 ቀን 2025 ዓ.ም. ድረስ ብቻ በዚህ ሊንክ https://forms.gle/XUiQinGVYaKBGdnUA ፎርሙን በመሙላት መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እናሣውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
የቢዝነስ ፎረሙ የሚካሄድበትን ቦታ፣ቀን እና ሰዓት ለተመዘገቡት ተሳታፊዎች ብቻ በአጭር መልዕክት ወይም በኢሜል ይገለጻል፡፡
ለበለጠ መረጃ 0911200786 / 0917809005 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡:

