ለንግድ ማኅበረሰብ በሙሉ – የኢትዮ-ሳዉዲ የቢዝነስ ፎረም ላይ እንዲትሳተፉ ስለመጋበዝ

ለንግድ ማኅበረሰብ በሙሉ ጉዳዩ፡- የኢትዮ-ሳዉዲ የቢዝነስ ፎረም ላይ እንዲትሳተፉ ስለመጋበዝ
—————————————————————————–
ህዳር 8 ቀን 2018 (ኖቨምበር 18 ቀን 2025) ከሳዉዲ አረቢያ ከሚመጡ በተለያዩ ግዙፍ የንግድ ዘርፎች የተሰማሩ ከ50 በላይ ባለሀብቶችን ያቀፈ የንግድ ልዑካን ቡድን እና ከኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ ጋር የቢዝነስ ፎረም ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በቢዝነስ ፎረሙ በሚደረገዉ የንግድ ከንግድ (Business to Business-B2B) ዉይይቶች ለሀገራችን የንግድ ማህበረሰብ ለሀገራችን ምርቶች አማራጭ የገበያ እድል ይፈጥራል፡፡
ይህ ፎረም ሳዉዲ አረቢያ ከአገራችን ጋር ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ትብብር ለማጠናከር እድል የሚፈጥር መሆኑ ይታመንበታል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ የንግድ ዘርፍ ማለትም በላኪ እና አስመጪነት፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣በማኑፋክቸሪንግ፣በማእድን፣በፋርማሲዉቲካልስ፣በኢንጂነሪንግ፣በታዳሽ ሃይል፣ እና መሰል የንግድ ዘርፎች የተሰማራችሁ የሀገራችን የንግድ ማህበረሰብ በሙሉ፤ በቢዝነስ ፎረሙ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ እስከ ህዳር 3 ቀን 2018 ብቻ በዚህ ሊንክ https://forms.gle/6VDf2s9mtH2DPwuP8 ፎርሙን በመሙላት እንዲትመዘገቡ ተጋብዛችኋል፡፡
ቦታና ሰአት ——-ለተመዝጋቢዎች ብቻ በስልክና በአጭር መልእክት ይገለጻል፡፡
ለበለጠ መረጃ—- 0911200786 / 0917809005 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

