Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Mar 20, 2026 .

ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ-ኮሜርስ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች በዲጂታል ማርኬቲንግና ኢ-ኮሜርስ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የሥልጠናው  ማጠቃለያ  ላይ የተገኙት የምክር ቤቱ የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር አቶ ብሥራት በለጠ ወጣቶች በሥራ ላይ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮች ለመፍታት በየጊዜው በሚሰጡ  ስልጠናዎች ራስን ማብቃት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ስልጠናው ለወጣቶች ዘመናዊ አሰራርና ግብይትን እንዲያውቁ እንዲሁም ምርትና አገልግሎታቸውን በቀላሉ ለደንበኞቻቸው ማድረስ እንደፊችሉ ያግዛል ተብሏል፡፡

ምርትና አገልግሎቶች ለአካባቢያዊ፣ ለቀጣናዊና አለም አቀፍ ገበያ በቀላሉ ለመድረስ አጋዥ እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡
ሰልጣኞችም ያገኙት ስልጠና ዘሙን የሚመጥንና በስራቸው ላይ ለውጥ ለማምጣት አጋዥ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡ ለሰልጣኞቹም ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በቢዝነስ አመራር አካዳሚው በኩል በተለያዩ የስልጠና መስኮች ፍላጎትን መሰረት በማድረግ በተለይም ለሴቶች፣ ለወጣቶችና ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia