Feb 26, 2025 .
ሪአኒሜድ የተሰኘው የተርኪዬ ኩባንያ በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡
ሪአኒሜድ የተሰኘው የተርኪዬ ኩባንያ በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡ የኩባንያው የቦርድ አባል ዶክተር ኤልያስ ኬስኪን ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኩባንያው የህክምና ቁሳቁሶችን በማምረት ለጤና ተቋማት የሚያቀርብ ሲሆን በአፍሪካም እንደ ጋና፣ ኮንጎ እና ኬንያ ባሉ ሀገራት እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡
ዋና ጸሐፊው ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍም ሆነ በሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮች ያለውን የኢንቨስትመን እድል አብራርተውላቸዋል፡፡
ሪአኒሜድ ሄልዝ ኬር ሲስተም የተሰኘው ኩባንያ ከህክምና ቁሳቁሶች ማምረት በተጨማሪ ባሉት እህት ኩባንያዎች አማካኝነት በግብርና እና በኃይል አቅርቦት መስኮችም በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ፍላጎት እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
