Feb 26, 2025 .
ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በቡና ዙሪያ ከሚሠራው የኬንያው ካፕ ኦፍ ጆ (cup of Joe) ኩባንያ ጋር ተወያዩ።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በቡና ዙሪያ ከሚሠራው የኬንያው ካፕ ኦፍ ጆ (cup of Joe) ኩባንያ ጋር ተወያዩ።
ኩባንያው ከኬንያ ባለፈ በዱባይ እና በሩሲያ በቡና ንግድ ላይ የሚሰራ ተቋም ሲሆን በኢትዮጵያም ከቡና አምራችና ላኪ ኩባንያዎች ጋር በጋራ መስራት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
ምክር ቤቱም የንግድና ኢንቨሥትመንት ትስስር ለመፍጠር እንደሚሰራ አስታውቆ የኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ለሁለቱ ሀገራት የቡና ገበያ መልካም እድል መሆኑን ተገልጧል።
በውይይቱም የኢትዮጵያ ቡና ማህበርን ጨምሮ እንደ ቶሞካ እና ፊሊ ቡና ያሉ በቡና ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎችም ተሳትፈዋል፡፡

