በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤትና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለሴት የቢዝነስ ባለቤቶች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ።


በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤትና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለሴት የቢዝነስ ባለቤቶች ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ተጠናቀቀ።
“Global Female Enterpreneurship Empowerment Programm- Ethiopia Workshop ” በሚል የተሠጠው ሥልጠና የሴቶችን ቢዝነስና ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ነው።
በሥልጠና ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ፣ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ተወካዮች፣ የአዲስ ቻምበር፣ የCCECC ኢትዮጵያ ኮንሥትራክሽን PLC እንዲሁም የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ ተወካዮችና እንግዶች ተገኝተዋል።




ሥልጠናው ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል እውቀትና ግንዛቤ የተገኘበትና ወደ ተግባር መቀየር የሚችል ሲሆን የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ቻይናን የላቀ ትብብር የሚያሳይ መሆኑን አቶ ጸደቀ ድጋፌ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።
“Global Female Enterpreneurship Empowerment Programm ዳይሬክተር ሁ ሮሚ ሥልጠናው የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ ያለመ የቻይና ዓለም አቀፍ ኢንሼቲቭ አካል መሆኑን አብራርተዋል።
ለግማሽ ወር ያክል ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በቢዝነስ ሥትራቴጂያዊ፣ በቢዝነስ ሞዴል እንዲሁም ከቻይና ገበያ ጋር በተያያዘ ያሉ የቢዝነስ እድሎችን በሚዳስሱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ቡና፣ አልባሣትና የቆዳ ውጤቶችን ጨምሮ በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች ላይ ተሰማሩ ከ60 በላይ ሴት የቢ ዝነስ ባለቤቶች በሥልጠናው ላይ ተሣትፈዋል።
የተለያዩ የሴቶች የቢዝነስ ተቋማትም ከCCECC ኢትዮጵያ ኮንሥትራክሽን PLC እና ከGlobal Female Enterpreneurship Empowerment Program ጋር አብሮ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።


ሥልጠናው የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ እና CCECC ኢትዮጵያ ኮንሥትራክሽን PLC ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከአዲስ ቻምበር እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
ከስልጠናው ጎን ለጎን ሠልጣኞቹ የቢነዝስ ተቋማቱን የምርትና አገልግሎቶቻቸውን ለእይታ አቅርበዋል። ሥልጠናውን ለተከታተሉ ሠልጣኞችም የማጠናቀቂያ የምሥክር ወረቀት ተሠጥቷቸዋል።


Ethiopian Female business entrepreneurs in Addis Ababa completed training offered by Beijing Foreign Studies University in collaboration with the Ethiopian Chamber of Commerce, sectoral associations, and other stakeholders.
The workshop, which is entitled “Global Female Entrepreneurship Empowerment Programme- Ethiopia Workshop,” aims to promote women’s business and economic engagement.
The training completion program was attended by Mr. Tsedke Degafe, Deputy Secretary General of the Ethiopian Chamber of Commerce and sectoral associations, as well as representatives from Beijing Foreign Studies University, the Chinese Embassy in Ethiopia, Addis Chamber, CCECC Ethiopia Construction PLC, and other invited guests.
In his remarks during the program, Mr. Tsedeke Digafe stated that the training provided practical knowledge and understanding that can be put into practice, demonstrating Ethiopia, Africa, and China’s strong partnership.
Global Female Entrepreneurship Empowerment Program Director Hu Ruomei explained that the training is part of China’s global initiative aimed at increasing women’s economic empowerment.
The training, which ran around half a month, focused on business strategy, business models, and potential in the Chinese market.
More than 60 female company owners from a variety of industries, including coffee, textiles, and leather items, attended the workshop.
Some women entrepreneurs have also signed a Memorandum of Understanding (MoU) for cooperation with CCECC Ethiopia Construction PLC and the Global Female Entrepreneurship Empowerment Programme.
The training was organized by Beijing Foreign Studies University and CCECC Ethiopia Construction PLC in partnership with the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations, Investment commission, Addis Chamber, and other stakeholders.
Along with the training, trainees exhibited their businesses’ products and services.
The participants who attended the training were awarded certificates of completion.

