Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 20, 2025 .

ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከኬንያ የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ካቢኔ ሲክሬተሪ ክቡር ሊ ኪንያንጂዩን ጋር በኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

 

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከኬንያ የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ካቢኔ ሲክሬተሪ ክቡር ሊ ኪንያንጂዩን ጋር በኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ እ.ኤ.አ ሚያዚያ 17 ቀን 2025 በኬንያ ሞምባሳ የደረስንበት ስምምነት አካል ሲሆን በሁለቱ ጎረቤት አገራት መካከል ለረጅም ጊዜ የወዳጅነት እና የሁለትዮሽ ትብብር ታሪክ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ የሚኖረው ነው ሲሉ ዶ/ር ካሳሁን ገልፀዋል፡፡

ይህ የንግድ ስርዓት ስምምነት የንግድ እንቅፋቶችን በመቀነስ አነስተኛ መጠን ያለው ድንበር ተሻጋሪ ንግድን የሚያጠናክር ነው ያሉት ሚኒስትሩ በተለይም በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዎቹን መደበኛ ያልሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች በተለይም ለሴቶች እና ወጣቶች ግልጽና ሊገመት የሚችል ማዕቀፍ የሚፈጥር ነውም ብለዋል፡፡

የጉምሩክ አሠራሮችን ቀላል በማድረግ እና ሰነዶችን በማስማማት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ህጋዊ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ያደርጋል ያሉ ሲሆን ይህ ስምምነት ወደ ሙሉ ትግበራ ሲገባ የንግድ ዕድሎችን የሚያሰፋ ሲሆን የሁለቱ ሃገራት መንግስታትና የግሉ ዘርፍ በጠንካራ ቅንጅት መስራት ይኖርብናልም ብለዋል።

የኬንያ ልኡካን ቡድን በቆይታቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የወጪ ንግድ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia