Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com
Latest News
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባል ምክር ቤቶችን ተቋማዊ አቅም እንዲሁም የአሠራር ብቃትን ለማጠናከር የጀመረውን የአቅም ግንባታ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እያከናወነ ነው። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በተካሄደው 8ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ ተገለጸ። በንግድ ዘላቂነት እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት ስትራቴጂካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቋል። የካፒታል ጋዜጣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ሰፊ፣ዝርዝርና ሙያዊ ቆይታ አድርጓል። በተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራውና የምክር ቤቱን የቦርድ አባላት ያካተተው ልዑክ፣ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በኤግዚቢሽኑ ተሳትፏል። ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ማኅበረሰብ ጋር ማገናኘት የውጭ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉብኝቶቻችን ዋነኛ ዓላማ ነው።

Read more

Nov 13, 2026 .

በንግድ ዘላቂነት እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት ስትራቴጂካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከGIZ Step 4 ጋር በመተባበር ለአባል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤቶች ዋና ፀሐፊዎችና የአባላት ጉዳይ ዳይሬክተሮች በንግድ ምክር ቤት ሥርዓት ውስጥ የንግድ ዘላቂነት (Business Sustainability in the Chamber System) እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት (Membership Database System)” በሚሉ ሁለት ዋና ዋና እና ስትራቴጂካዊ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቋል።

ባለንበት የዲጂታል ዘመን ጠንካራ ተቋም ለመገንባት መረጃ ወሳኝ መሳሪያችን እንደመሆኑ መጠን የየምክር ቤቶቻችን አባላት ማን እንደሆኑ፣ ምን ዓይነት አገልግሎት እንደሚያስፈልጋቸው እና አቅማቸው ምን እንደሚመስል በዘመናዊ የመረጃ ቋት (Membership Database System)የተደገፈ መረጃ ከሌለን ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠትም ሆነ የአባላቶቻችንን ድምፅ በአግባቡ ማሰማት አንችልም።

በመሆኑም እያንዳንዱ አባል ምክር ቤት ዘመናዊ የዲጂታል አሰራርን በመተግበር የአባላቱን መረጃ በአግባቡ እንዲያደራጅና አገልግሎቱን ለማዘመን በአገር አቀፉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የበለፀገዉን የአባላት የመረጃ ቋት በአግባቡ መጠቀም አለባቸዉ ብለዋል የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ በስልጠናዉ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት።
በመጨረሻም አባል ምክር ቤቶች ጠቅላላ ጉባኤያቸዉ በተላለፈላቸዉ ሰርኩላር መሠረት እንዲያካሂዱ አሳስበዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia