Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com
Latest News
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባል ምክር ቤቶችን ተቋማዊ አቅም እንዲሁም የአሠራር ብቃትን ለማጠናከር የጀመረውን የአቅም ግንባታ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እያከናወነ ነው። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በተካሄደው 8ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ ተገለጸ። በንግድ ዘላቂነት እና የአባላት የመረጃ ቋት ሥርዓት ስትራቴጂካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተጠናቋል። የካፒታል ጋዜጣ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ጋር ሰፊ፣ዝርዝርና ሙያዊ ቆይታ አድርጓል። በተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራውና የምክር ቤቱን የቦርድ አባላት ያካተተው ልዑክ፣ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኩባንያዎችና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በኤግዚቢሽኑ ተሳትፏል። ኢትዮጵያን ከዓለም አቀፍ የንግድ ማኅበረሰብ ጋር ማገናኘት የውጭ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉብኝቶቻችን ዋነኛ ዓላማ ነው።

Read more

Nov 13, 2026 .

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በተካሄደው 8ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገው ድርድር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በተካሄደው 8ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ላይ ተገለጸ።

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር እና የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደቱ ዋና ተደራዳሪ ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ የተመራው የልዑካን ቡድን ስብሰባውን ጀምሯል። ክብርት ሚኒስትሯ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳስገነዘቡት፣ የድርጅቱ አባልነት ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር አካል ሲሆን፣ የቅድሚያ ትኩረት ከተሰጣቸው ተግባራት አንዱ ነው።

የሀገራችን የድርጅቱ አባል መሆን የፖሊሲ ቀጣይነትን እና ግልጸኝነትን ከማጠናከሩም በላይ፣ ምርትና ምርታማነትን፣ የውጭ ንግድን እና ኢንቨስትመንትን በማስፋት የሥራ ዕድልን ለመፍጠር አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው።

ከባለብዙ ወገን ስብሰባው ጎን ለጎን፣ የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ተካሂዷል። ከሁለቱም ወገኖች ጋር የተካሄደው ድርድር እጅግ ፍሬያማ ነበር። እስካሁን ለሁለትዮሽ ድርድር የጠየቁ 17 ሀገራት ሲሆኑ፣ ከ11 ሀገራት ጋር ስምምነት ተፈርሟል።

የድርድር ቡድኑ ቀሪ ባለብዙ ወገን የእንጥልጥል ጉዳዮችን በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።

ክብርት ሚኒስትር ያስሚን ወሀብረቢ በማጠቃለያ ንግግራቸው፣ የተገኘውን ፍጥነት ለመጠበቅ እና ድርድሮችን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ ተሳካ መደምደሚያ ለማድረስ ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት፣ የጋራ ኃላፊነት እና በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል የቀጠለ ትብብር እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

8ኛው ዙር ድርድር እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 9-10 ቀን 2026 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በጄኔቫ እየተካሄደ ይገኛል።( የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር)

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia