Nov 13, 2026 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባል ምክር ቤቶችን ተቋማዊ አቅም እንዲሁም የአሠራር ብቃትን ለማጠናከር የጀመረውን የአቅም ግንባታ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እያከናወነ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአባል ምክር ቤቶችን ተቋማዊ አቅም እንዲሁም የአሠራር ብቃትን ለማጠናከር የጀመረውን የአቅም ግንባታ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እያከናወነ ነው።
ጠንካራ፣ ተወዳዳሪና ዘላቂ ውጤትን ማሳካት ዓላማው ያደረገ የአባላት አቅም ግንባታ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ቁልፍ ተልዕኮና ቀጣይነት ያለው ተግባራችን ሲሆን ዛሬ የተናቀቀው መድረክም የዚሁ ጥረታችን አንድ አካል ነው።
የአባል ምክር ቤቶች የአመራር ብቃትን እና ሁሉ አቀፍ የአባላት ተሳትፎን ማጠናከር ለጠንካራ የግሉ ዘርፍ ውክልናና ለሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ወሳኝ ነው።
ስለሆነም፤ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፤ በምክር ቤታችን በኩል ከምናደርገው ጥረት ባሻገር ራሳቸሁን በራሳችሁ የማብቃት አቅጣጫ በተግባር እንድታሳኩ የሚያስፈልጉ ድጋፎችን፣ የአቅም ግንባታና የትብብር ስራዎችን በቀጣይነት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

