Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 26, 2025 .

በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ጥናት ቀረበ።

  

በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ጥናት ቀረበ።
በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) ውስጥ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ያለውን ጉዞና የፖሊሲ ማሻሻያ በተመለከተ የተዘጋጀ ስትራቴጂካዊ ጥናት ይፋ ሆኗል።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት እና በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ትብብር የተካሄደው ይህ ጥናት “የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራየዞችን ተወዳዳሪነት ፖሊሲና የቁጥጥር ስርዓትን በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ የኢትዮጵያ ጉዞ”  በሚል ርእስ ዛሬ ለውይይት ቀርቧል፡፡

 
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሀኪም ሙሉ (ዶ/ር) በውይይት መድረኩ ባደረጉት ንግግር AfCFTA ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አፅንዖት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የብሔራዊ ስትራቴጂ ነድፋለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በስትራቴጂው ከተለዩት ሰባት ዋና ዓላማዎች መካከል “በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተሰማሩ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ሌሎች ተጋላጭ ማህበረሰብ ቡድኖች” በአህጉሩ ነጻ ንግድ ቀጣና በተፈጠሩ የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ዋነኛው መሆኑን አስረድተዋል።
ይህንን ዓላማ ለማሳካትና በሂደቱ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የቀረበው ጥናት ጠቃሚ መሆኑንም ገልጸዋል።
በውይይቱ በሀገሪቱ የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ውስጥ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ዋና ዋና ምክረ-ሃሳቦች ቀርበዋል።
አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራየዞች ምቹ የዲጂታል አሰራርን እንዲከተሉ ማበረታታት፣ ደራሽ የሆነ የገበያ መረጃ እና የንግድ እድሎችን ጭምር ማስተሳሰር የሚችሉ መንገዶችን ማቅረብ የሚሉት ከተሰጡ ምክረ ሀሳቦች ውስጥ ይገኙበታል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia