በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በሶማሌላንድ የንግድ ምክር ቤት መካከል የመግባብያ ስምምነት ተፈራርመናል- የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በሶማሌላንድ የንግድ ምክር ቤት መካከል ንግድና ኢንቨስትመንት ማስፋፋት ዙሪያ በጋራ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የመግባብያ ስምምነት ተፈራርመናል።
ስምምነቱ ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር፣ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የንግድ ግንኙነቶችን እንዲያሳድጉ፣ አዳዲስ የገበያ ዕድሎችን እንዲያገኙ እና የጋራ ኢንቨስትመንት አቅሞችን እንዲያስፋፉ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያግዝ ነው።
በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ምክር ቤቶች የንግድ መረጃ ልውውጥን ማሳደግ፣ የንግድ ልዑካን ጉብኝቶችንና የንግድ ቢዝነስ ፎረሞችን ማመቻቸት፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለባለሀብቶች ማስተዋወቅ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በጋራ ፕሮጀክቶችና የንግድ አጋርነቶች ላይ እንዲሳተፉ የሚያግዙ ተግባራትን በጋራ ለማከናወን የሚያስችል የትብብር ማዕቀፍ ይፈጥራል።
በተጨማሪም፣ ስምምነቱ በንግድና በኢንሹራንስ ዘርፎች የልምድና ዕውቀት ልውውጥን ለማበረታታት፣ በንግድ ሥራ ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመለየትና መፍትሔዎችን ለማፈላለግ ያስችላል።
የተፈራረምነው የመግቢያ ስምምነት ከዚህም ባሻገር የንግድ ማኅበረሰቦች መካከል ዘላቂ የንግድ አጋርነት መፍጠር፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ፣ የገበያ ተደራሽነትን ማስፋፋትና አዳዲስ የኢኮኖሚ ትብብር ዕድሎችን ማሳደግ ያስችላል።
ይህ የመግባቢያ ስምምነት በንግድ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ከመደበኛ ግንኙነት ወደ ተግባራዊ የንግድ ውጤት ለማሸጋገር፣ የግሉ ዘርፍን የኢኮኖሚ ልማት ሞተርነት ለማጠናከርና በክልሉ የጋራ ብልጽግናን ለማሳደግ ጠቃሚ እርምጃ ነው።
በዚህ አጋጣሚም፤ ለሶማሌላንድ የንግድ ምክር ቤትን እና አመራሮች በምክር ቤታችን ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት
❇️❇️❇️❇️❇️
On the sidelines of the Somaliland Insurance Summit and Expo 2026, which is now in its second day, the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) and the Somaliland Chamber of Commerce, Industry and Agriculture have signed a Memorandum of Understanding (MoU) to cooperate on matters of mutual interest aimed at promoting trade and investment.
The agreement is designed to strengthen cooperation between the institutions, enabling private sector actors to expand business relationships, access new market opportunities and explore opportunities for joint investment.
Under the agreement, the chambers will establish a framework for cooperation that will facilitate the exchange of trade information, organise business delegations and business forums, promote investment opportunities to investors, and support private sector representatives in participating in joint projects and business partnerships.
Furthermore, the agreement will encourage the exchange of knowledge and experience in the trade and insurance sectors, while enabling the two chambers to jointly identify challenges facing businesses and explore practical solutions.
Beyond these areas, the MoU is expected to foster sustainable business partnerships between the business communities, enhance private sector participation, expand market access and create new opportunities for economic cooperation.
The signing of this MoU marks an important step towards transforming institutional cooperation from formal engagement into tangible business outcomes, strengthening the private sector’s role as an engine of economic development and advancing shared prosperity across the region.
On this occasion, I would like to express my sincere appreciation, on behalf of our Chamber, to the Somaliland Chamber of Commerce and its leadership for their cooperation and commitment to strengthening our partnership.
H.E. Sebsib Abafira Abajobir, President,
Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

