Oct 28, 2025 .
ባለፈው አመት ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢኮኖሚን በተመለከ ያንሷቸው ነጥቦች….
ባለፈው አመት ግብርና ብቻውን የ7 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።
የቡና ምርትን ከነበረበት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ባለፈው ዓመት 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስ ተችሏል፤
ቡና በሀገር ውስጥ ያለውን ፍላጎት ሸፍኖ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ንግድ ተገኝቷል፤
ሩዝን ከነበረበት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 63 ሚሊዮን ኩንታል ማሳደግ የተቻለ ሲሆን የስንዴ ምርትንም ከለውጡ በፊት ከነበረበት 47 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 280 ሚሊዮን ኩንታል በአጠረ ጊዜ ውስጥ አሳድግነዋል።
ያለፈው በጀት ዓመት ከሸቀጦች ወጪ ንግድ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል።
ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትም በቢሊዮን ዶላር ማዳን ተችሏል። በዚህም የኢትዮጵያ ሪዘርቭ በ10 እጥፍ አድጓል።
የዚህ አመት የጥቅምት ወር የዋጋ ንረት 11 ነጥብ 7 በመቶ ወርዷል።
ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2032 በአፍሪካ 2ኛ በ2036 ደግሞ ከአፍሪካ የመጀመሪያውን ኢኮኖሚ ይኖራታል።

