Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 05, 2025 .

አቶ ሰብስብ አባፍራ አባጆብርና ዋና ፀሐፊዉ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከኢፌዴሪ  የግብርና ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ ጋር በፅ/ቤታቸዉ ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፍራ አባጆብርና ዋና ፀሐፊዉ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ምክር ቤቱ ከግብርና ሚንስቴር ጋር ተቀናጅቶ መስራት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ከኢፌዴሪ  የግብርና ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ ጋር በፅ/ቤታቸዉ ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፍራ አባጆቢር  ስለ ምክር ቤቱ ዓላማና ተልዕኮ ለክቡር ሚንስትሩ በዝርዝር አስረድተዉ የግብርና ዘርፉ ከምክር ቤቱ ጋር ተቀናጅቶ መስራት ለአገር ኢኮኖሚ ግንባታ ያለዉ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑንም አብራርተዋል።

የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸዉ የግብርና ሚንስቴር ከምክር ቤቱ ባለድርሻ አካላት አንዱ መሆኑን በመጠቆም ከፊታችን ጥር 27 እስከ የካቲት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የንግድ ምክር ቤቱ ለሚያዘጋጀዉ 15ኛዉ አለም አቀፍ ኢትዮ ቻምበር የንግድ ትርኢት ሚ/ር መስርያ ቤቱ ባለድርሻ አካላቱን እንዲያሳትፍም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢፌዴሪ ግብርና ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ በበኩላቸዉ በግብርናዉ ክፍለ ኢኮኖሚ ተሰማርተዉ የተለያዩ ምርቶችን በማምረት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እሴት ሊጨምሩ ወደሚችሉ ዘርፎች በመሸጋገር ወደ ንግዱም እንዲገቡ ስለምንፈልግ ከምክር ቤቱ ጋር ተቀናጅተን ለመስራትና አስፈላጊዉን እገዛ ለማድረግም ዝግጁ ነን ብለዋል።

ምክር ቤቱ እያዘጋጀ ባለዉ 15ኛዉ አለም አቀፍ የኢትዮ ቻምበር የንግድ ትርኢት ላይም የግብርና ምርት አምራቾችና የግብርና ግብአት አቅራቢዎችን እንደሚያሳትፉም አሳዉቀዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia