Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 01, 2026 .

ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤለተሰጥዎት ከፍተኛ ኃላፊነት በድጋሜ እንኳን ደስ አለዎት – ሰብስብ አባፊራ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው የመንግሥት ምስረታና የአራተኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ እንደገና የከተማችን ከንቲባ ሆነው እንዲያገለግሉ በመሰየማቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፋ።

ፕሬዚደንቱ በመልዕክታቸው ከተማችን ባለፉት ዓመታት በእርስዎ አመራር ሰጪነት በተከናወኑ የከተማ ልማት ስራዎች ገጽታዋ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋም ጭምር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን አስችሏታል ብለዋል።

በይበልጥም ፤ በመዲናችን የተከናወኑ የኮሪደር ልማትና ተያያዥ የከተማ መሠረተ ልማት ሥራዎች የከተማዋን ውበትና የነዋሪዎቿን የኑሮ አካባቢ ከማሻሻል ባሻገር የግሉ ዘርፍ አንኳር ምሶሶዎች የሆኑት የንግድ እንቅስቃሴ፣ ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ እንዲስፋፉና እንዲጠናከሩ ያገዙ በመሆኑ ምስጋናችንን እናቀርባለን ያሉት ፕሬዚደንቱ:-

ከዚህም ባሻገር ፤ የኮሪደር ልማት ትርጉሙ መንገድና የከተማ ገጽታን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎችን ከገበያ፣ ንግዶችን ከደንበኞች፣ አምራቾችን ከገበያ መዳረሻዎች እና ኢንቨስተሮችን ከአዳዲስ ዕድሎች ማገናኘት ነው። ይህም የግሉ ዘርፍ እንዲያድግ፣ የንግድ ወጪዎች እንዲቀንሱ፣ የንግድ ቦታዎች እንዲበለጽጉና ከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማዕከልነቷን እንድታጠናክር በእጅጉ ያገዙ ናቸው።

በመሆኑም፤ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትም ሆነ በየደረጃው የሚገኙ አባል ምክር ቤቶች ፣ የአዲስ አበባ የኢኮኖሚ እድገትና የንግድ ማዕከልነት ከግሉ ዘርፍ ጠንካራ ተሳትፎ ጋር የተቆራኘ መሆኑን እናምናለን። ስለሆነም በቀጣዩ የአመራር ዘመንዎ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት በመስራት፤ የንግድ ማኅበረሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር፣ የኢንቨስትመንትና የንግድ ሥራ አካባቢን በማሻሻል እና የከተማዋን ኢኮኖሚ የበለጠ ለማሳደግ የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።

በመጨረሻም ለተሰጥዎት ከፍተኛ ኃላፊነት በድጋሜ እንኳን ደስ አለዎት እያልኩኝ በቀጣዩ የአመራር ዘመንዎም የበለጠ ስኬት እመኝልዎታለሁ ሲሉ አጠቃለዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia