Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 11, 2026 .

ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ፤ እርስዎ የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ሆነው በመሾምዎ እንኳን ደስ ያልዎት ለማለት እወዳለሁ- የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ

ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ፤

እርስዎ የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ሆነው በመሾምዎ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣  በመላው የንግዱ ማኅበረሰብ እንዲሁም በራሴ ስም  እንኳን ደስ ያልዎት ለማለት እወዳለሁ።

የእርስዎ መንግስታዊ ኃላፊነት፤ ለአገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት መስፋፋትና የግሉ ዘርፍ  ተሳትፎ ወሳኝ በሆነበት ወቅት የተሰጠ ከፍተኛ አገራዊ አደራ በመሆኑ፣ በአዲሱ የስራ ዘመንዎ የተሟላ  ውጤታማነትን እንዲጎናፀፉ ከልብ እመኛለሁ። በዚሁ አጋጣሚም ፤ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በሚኒስቴር መስሪያ ቤትዎ መካከል ያለው የትብብር ግንኙነት በቀጣይ ይበልጥ እንደሚጠናከርና ወደ ተግባራዊ ውጤቶች እንደሚሸጋገር ያለኝን እምነት እገልጻለሁ።

በተለይም የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ ዝግጅትና አፈፃፀም ያለውን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የንግድ ስራ ምቹ ሁኔታዎችን ማሻሻል፣ የንግድ ስርዓቶችን ማዘመን፣ የውጭ ንግድና የኤክስፖርት አቅምን ማሳደግ፣ የኢትዮጵያ ምርቶችና አገልግሎቶች በዓለም ገበያ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ማጠናከር እንዲሁም አገራችን በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ የንግድ ትስስር ያላትን ተሳትፎ ማሳደግ በጋራ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ቁልፍ የሥራ መስኮች መካከል ናቸው።

እነዚህን ዓላማዎች ለማሳካት ምክር ቤታችን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤትዎና ከሌሎች ተዛማጅ ተቋማት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ ያረጋግጣል። ምክር ቤታችንና መላው የንግዱ ማኅበረሰብ የሚያነሷቸውን ጉዳዮች በተቀናጀ መንገድ ለማቅረብ፣ ለተለዩ የንግድ እንቅፋቶች ዘላቂ መፍትሔ ለማፈላለግ፣ የጋራ የልማት አጀንዳዎችን ለመለየት እንዲሁም የተወሰኑ ውሳኔዎችን ውጤታማነት በጋራ ለመከታተል የሚደረገው ትብብር አስፈላጊ ነው።

በዚህ ረገድ ፤ ምክር ቤታችን በአባል ምክር ቤቶችና በየዘርፉ በሚንቀሳቀሱ የንግድ ማኅበራት የሚነሱ ጥያቄዎችንና ምክረ ሐሳቦችን በማሰባሰብ፣ በማጥናትና በማቅረብ ለጋራ መፍትሔ ለመሥራት ዝግጁ ሲሆን ፤ ይህም በቀጣይ ያለንን ግንኙነት የበለጠ ውጤታማ፣ ተቋማዊና ዘላቂ እንደሚያደርገው እምነቴ ነው። የአገራችን ኢኮኖሚያዊ ለውጥና ዘላቂ ብልፅግና የሚጠይቀው የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ጠንካራ አጋርነት፣ ግልጽ የፖሊሲ ውይይት፣ ተቀናጅቶ መሥራትና የጋራ ኃላፊነትን መወጣት ነው።

በዚህ ረገድ ምክር ቤታችን የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እንዲጠናከር፣ የንግድ ማኅበረሰቡ የልማት አጋርነት እንዲጎለብትና ለአገራዊ ኢኮኖሚያዊ ዓላማዎች መሳካት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ እንዲያድግ ከእርስዎ ጋር በቅርበት ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሜ  ያረጋግጣል። በመጨረሻም፣ ይህንን ከፍተኛ አገራዊ ኃላፊነት በብቃት፣ በታማኝነትና በስኬት እንዲወጡ ከልብ እመኛለሁ።

ምክር ቤታችን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤትዎ ጋር ያለውን የትብብር ግንኙነትም ከላይ እንደገለፅኩት በቀጣይ የበለጠ በማጠናከር፣ ለኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት፣ ለግሉ ዘርፍ ተወዳዳሪነትና ለአገራችን ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና የጋራ ዓላማዎቻችንን ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ እያረጋገጥኩ፣ በኃላፊነት ዘመንዎ  ሁሉ የተሟላ ስኬትን እመኝልዎታለሁ።

የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia