Nov 07, 2025 .
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄዱ::

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በቀጣይ የስራ ግንኙነቶች ላይ ውይይት አካሄዱ::
የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት በዛሬው ዕለት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አዳዲስ ኃላፊዎች ጋር የትውውቅ ና የቀጣይ የስራ ግንኙነቶች ላይ ውይይት አካሂደዋል ።
በውይይቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ባዩሽ ተስፋዬ ና ምክትል የቢሮ ኃላፊዎች ከክልሉ የንግድ ና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሳኒ ሀሰን እና ም/ፕሬዝዳንት አቶ ወንደሰን አርጋው እንዲሁም የቦርድ አባላቱ በተገኙበት በቀጣይ የቅንጅት ስራ ና ግንኙነት ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል ።(የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት)

