Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Dec 24, 2025 .

የማዕድን ሚኒስቴር በከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረትና የነዳጅ ስራዎች የጋራ ገቢ (ሮያሊቲ) አሰባሰብና ክፍፍል አፈጻጸም ላይ ከክልሎች ጋር የውይይት መደረክ አካሂዷል።

 

▶️ የማዕድን ሚኒስቴር በከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረትና የነዳጅ ስራዎች የጋራ ገቢ (ሮያሊቲ) አሰባሰብና ክፍፍል አፈጻጸም ላይ ከክልሎች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የውይይት መደረክ አካሂዷል።

▶️ በውይይቱ ላይ የክልል የማዕድን፣ የገቢዎች እና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

▶️ በመደረኩ ከዚህ በፊት የነበሩ አፈጻጸሞች ተገምግመው ወደፊት በጋራ ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮች ላይም አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

▶️ የማዕድን ሚኒስቴር በማዕድን ስራዎች አዋጅና ደንብ መሰረት ከከፍተኛ ደረጃ ማዕድን ማምረት ባለፈቃድ ኩባንያዎች የሚሰበሰበውን የጋራ ገቢ (ሮያሊቲ) ይሰበስባል።

▶️ ከአምራች ኩባንያዎች የተሰበሰበው ሮያሊቲ ገቢ በተፈቀደው የጋራ ገቢ ማከፋፈያ ቀመር መሰረት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ይከፋፈላል።

▶️ መደረኩ በፌዴራልና በክልል መንግስታት መካከል ትብብርን ለማጠናከር፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማሻሻል እንዲሁም የጋራ ገቢ አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል::

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia